በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራቅ ወታደራዊ ባለስልጣናት በራማዲ ከተማ የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ አውለበለቡ


የኢራቅ ወታደር በራማዲ ከተማ የሀገሪቱን ብሄራዊ ሰንደቅ አላማ በመንግሥት ህንጻ ላይ እያውለበለበ [ፎቶ አሶሽየተድ ፕረስ/AP]
የኢራቅ ወታደር በራማዲ ከተማ የሀገሪቱን ብሄራዊ ሰንደቅ አላማ በመንግሥት ህንጻ ላይ እያውለበለበ [ፎቶ አሶሽየተድ ፕረስ/AP]

የኢራቅ ወታደራዊ ባለስልጣናት ራማዲ ከተማን ከእስልምና መንግስት ተዋጊዎች ነጻ አውጥተን የሀገሪቱ ብሄራዊ ሰንደቅ አላማ በከተማዋ በዋናው የመንግሥት ህንጻ ላይ አውለብልበናል ሲሉ አስታወቁ።

ዛሬ ሰኞ የኢራቅ ሃይሎች የእስልምና መንግሥት ተዋጊዎች ከተማዋን ከመንጠቃቸው በፊት ያጠመዱት ፈንጂ ይኖር እንደሆን እያሰሱና ካለ በጥንቃቄ ጎዳናዎችን እያጸዱ ናቸው። የኢራቅ ወታደራዊ ባለስልጣናት ራማዲ ከተማን ከእስልምና መንግስት ተዋጊዎች ነጻ አውጥተን የሀገሪቱ ብሄራዊ ሰንደቅ አላማ በከተማዋ በዋናው የመንግሥት ህንጻ ላይ አውለብልበናል በማለትም አስታውቀዋል።

የእስልምና መንግስት ቡድን ሃይሎች የአንባር ክፍለ ሀገርዋን ዋና ከተማ የያዙዋት ባለፈው ግንቦት ወር ሲሆን የመንግስቱ ወታደሮች ትናንት እሁድ አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በሁዋላ ነው ወደ ዋናው የአስተዳደር ግቢ የገሰገሱት።

አሁንም የቀሩ ርዝራዥ ጂሃዳዊያን ሊኖሩ እንደሚችሉ ያልሸሸጉት የኢራቅ ሃይሎች ሆኖም ትናንት ከተማዋን የተቆጣጠሩዋት ከጂሃዳውያኑ በኩል አንዳችም ውጊያ ሳይገጥማቸው መሆኑን አመልክተዋል። በሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ተአማኒ የሆነ ሪፖርት አልተገኘም።

ከዋና ከተማዋ ከባግዳድ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ራማዲ መሃል ከተማ ምን ያህል ሰላማዊ ነዋሪ እንደቀረም በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። አንድ የመንግሥቱ አቀባይ እንዳሉት አብዛኛው ነዋሪ በአቅራቢያው ባለ ሆስፒታል ተጠልሏል።

የኢራቅ ሃይሎች ከወራት ዝግጅት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ መራሹ የአየር ጥቃት እየታገዙ ወደ መሃል ከተማዋ መገስገስ የጀመሩት ባለፈው ሳምንት ነው። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

የኢራቅ ወታደራዊ ባለስልጣናት በራማዲ ከተማ የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ አውለበለቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:23 0:00

XS
SM
MD
LG