በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለተስፋ ልጆች ተስፋ የሆናቸው - 231 ሺሕ ብር


ከሁለት ወራት በፊት ከሆቴሎች የሚገኙ የተራረፉ ምግቦችን እየተመገቡ ስለሚማሩ የሐረር ከተማ 40 ተማሪዎች ያቀረብነው ዘገባ ሰምተው ለልጆቹ በተለያየ መንገድ ዕርዳታ እንደተሰጣቸውና ያገኙት 231 ሺሕ ብርም ተስፋን እንደሆናቸው አሰባሳቢያቸው ነግሮናል። ልጆቹም ለተደረገላቸው እርዳታ ከልብ አመስግነዋል።

ለተስፋ ልጆች ተስፋ የሆናቸው - 231 ሺሕ ብር
please wait

No media source currently available

0:00 0:18:28 0:00

ለተስፋ ልጆች ተስፋ የሆናቸው - 231 ሺሕ ብር
please wait

No media source currently available

0:00 0:18:28 0:00


በዘገባውም ተስፋ ልጆቹን ትምሕርት ያስጀመረው እዛው ጎዳና ላይ እያደሩ ከሆቴሎች የሚገኙ የተራረፉ ምግቦችን እየተመገቡ መሆኑን ገልፆ አሁን ወደ መኖሪያ ቤት መግባታቸውና ትምሕርታቸውን እየተማሩ መሆኑን ገልፆ ተማሪዎች ተመልሰው እንዳይወጡ ለማድረግ ደግሞ የልብስ አጠባ አገልግሎት እና እንጀራ እየጋገሩ ለመሸጥ ዕቅድ መንደፉን ገልፆልን ነበር።

ተስፋ አለባቸው ከሰባት ዓመቱ ጀምሮ ብቸኝነትና የጎዳን ተዳዳሪነትን ሕይወትን የቀመሰው ሲሆን ራሱን ከችግር ጋር አስተምሮ ሥራ ከያዘ በኋላ ተመልሶ ወደ ጎዳና በመሄድ ሕፃናቱን ሰብስቦ ታሪኩን በመንገር ትምሕርታቸውን እንዲማሩ አግባብቷቸዋል።

ከእነዛ ተማሪዎች ውስጥ ቤተክርስቲያን ደጅ ላይ ለልመና ላስቲክ አንጥፈው በሚያገኙት ትርፍራፊ ምግብ ለሚያሳድጓት ማየት የተሳናቸው ወላጆቿ በቶሎ ለመድረስ ጠንክራ ከምትማር የ10ኛ ክፍል የደረጃ ተማሪ ጀምሮ፤ ቤተሰቦቻቸውን ከነመፈጠራቸው የማያውቁ በልጅነት ጊዜያቸው ብዙ መከራን የገፉ ተማሪዎች ሕይወት የተወሰኑትን በምሳሌነት አቅርበን አሰምተናችሁ ነበር።

በምሳሌነት መርጠን የሌሎቹን አርባ ተማሪዎች ይወክላሉ ስንል መብራቱ ታደሰ፣ የትነበርሽ አያሌው እና ግዮን ሽባባውን ሲሆን አንድ ደግሞ በውጭ ሆና ትምሕርቷን የምትከታተል ገሊላ ሰለሞን የተባለች ተማሪም አነጋግረን ነበር።

ይህንን የልጆቹን ታሪክ የሚተርከውን ዘገባ ባቀረብን ማግስት አንድ ጥሪ ከጄኔቫ ስዊዘዘርላን አገኘን ውሂብ የሽጥላ እንደሚባሉ ነግረውን በልጆቹ ታሪክ እጅግ ማዘናቸውንና መርዳት እንደሚፈልጉ ገልፀው ስልክ ጠየቁን የተሰፋን ስልክ ሰጠናቸው። በርካታ ሰዎች በኢሜል አድራሻ ጠየቁንን በተጨማሪም በፌስቡክ ገፃችን ላይ በጋራ ሆነውነው በጎ ፈንድሚ ገንዘብ ለመሰብሰብ ጠይቀውን ነበር። በተጨማሪ ደግሞ በፕሮግራሙ ላይ ከተሰማው ታሪክ ውስጥ ገሊላ ሰለሞን የተባለችው ተማሪ ታሪክ እንዳሳዘናቸው ለገለፁ ከ30 በላይ ሰዎች ስልክ ቁጥር ሰጠን።

ተስፋ አለባቸው በዚህ ምክኒያት በርካታ የስልክ ጥሪዎችን እንዳስተናገደ እና በፕሮግራሙ ላይ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ የስልክ ጥሪ እንዳገኘ ነገረን።

አቶ ውሂብ እሳቸውን ጨምሮ በጄኔቫ የሚገኙና እንዲህ ያሉ በጎ ሥራዎችን ለመስራት “በጄኔቫ የኢትዮጵያውያን የቤተሰብ ጉባኤ ስብስብ” በሚል የተሰባሰቡ ጓደኛና ቤተሰባማቾች በጋራ ሆነው 130 ሺሕ ልከውለታል። በፌስ ቡክ “ጎ ፈንድ ሚ” ላይ የተሰበሰበው 105 ሺሕ ብርም እንዲሁ ደርሶታል። ተጨማሪ ርዳታዎችንም ማግኘታቸውን ተናግሯል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG