የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ሃብታሙ ሀብታሙ አያሌው ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መምሪያ በነበረበት ወቅት፤ የጀመረው ሕመም ተባብሶ ራሱን መርዳት በማይችልበት ሁኔታ በሆስፒታል አልጋ ላይ እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ በትናንትናው ዕለት ለአሜሪካ ድምጽ መግለጻቸው ይታወሳል።
በሀገር ውስጥ የሚገኘው ሕክምናም ለሌላ ስቃይ የሚዳርገውና ሕይወቱን ለአደጋ የሚጥለው እንደሆነ በመግለፅ ከአገር ወጥቶ መታከም እንዲችል ቢጠይቅም ፍርድ ቤት በጣለበት እግድ ምክንያት ከሀገር መውጣት እንዳልቻለና ይህ እግድ እንዲነሳለት በጠበቃው አቶ አመሐ መኮንን አማካኝነት በትናንትናው ዕለት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አስገብተው ዛሬ ይታያል መባላቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።
በዛሬው ዕለት የእግድ ይነሳልን አቤቱታ የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ አቶ ሀብታሙ በሀገር ውስጥ መታከም እንደማይችልና ሕክምናውን ከሀገር ውጪ ማድረግ አለበት የሚል በዶክተሮች የተወሰነ ማስረጃ ካቀረባችሁ በማንኛውም ሰዓት እግዱ ይነሳል እንደተባሉ ጠበቃው አቶ አመሐ መኮንን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።