ዋሽንግተን —
የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ሀብታሙ አያሌው ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መምሪያ በነበረበት ወቅት፤ የጀመረው ሕመም ተባብሶ ራሱን መርዳት በማይችልበት ሁኔታ በሆስፒታል አልጋ ላይ እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ ገለጹ።
ሀብታሙ በሀገር ውስጥ የሚገኘው ሕክምናም ለሌላ ስቃይ የሚዳርገውና ሕይወቱን ለአደጋ የሚጥለው እንደሆነ በመግለፅ ከአገር ወጥቶ መታከም እንዲችል ቢጠይቅም ፍርድ ቤት በጣለበት እግድ ምክንያት መውጣት እንዳልቻለ ቤተሰቦቹ ገልጸዋል። በዛሬው ዕለትም የእግዱ ይነሳልኝ አቤቱታ በድጋሚ ለፍርድ ቤት ማስገባታቸውን ይናገራሉ።
ጽዮን ግርማ የአቶ ሃብታሙን ቤተሰቦችና ጠበቃውን አቶ አመሐ መኮንን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።