በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ፓኪስታን በሚገኝ ዩኒቨርስቲ አጥቂዎች ቦምብ አፈንድተው ቢያንስ ሃያ አንድ ሰዎች ገድለዋል

ፓኪስታን በሚገኝ ዩኒቨርስቲ አጥቂዎች ቦምብ አፈንድተው ቢያንስ ሃያ አንድ ሰዎች ገድለዋል


ሰሜን ምዕራብ ፓኪስታን በሚገኝ ዩኒቨርስቲ ዛሬ ረቡዕ አጥቂዎች ተኩስ ከፍተውና ቦምብ አፈንድተው ቢያንስ ሃያ አንድ ሰዎች መግደላቸው ተገለጠ

ሰሜን ምዕራብ ፓኪስታን በሚገኝ ዩኒቨርስቲ ዛሬ ረቡዕ አጥቂዎች ተኩስ ከፍተውና ቦምብ አፈንድተው ቢያንስ ሃያ አንድ ሰዎች መግደላቸው ተገለጠ።

ብዙዎች መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናትና የሆስፒታል ምንች ገልጸዋል።

ባለስልጣናቱ "ሽብርተኞች" ሲሉ የገለጿቸው አጥቂዎች ቻርሳዳ በተባለችው ከተማ የሚገኘው ባቻ ዩኒቨርስቲን ወረው በተማሪዎችና መምህራን ላይ ተኩስ ከፍተዋል።

የፓኪስታን ታሊባን ቃል አቀባይ በዩኒቨርስቲው ላይ በደረሰው ጥቃት እጃችን የለበትም፣ ወታደራዊ ያልሆኑ ተቋማትን የጥቃት ዒላማ አናደርግም ሲል ለቪኦኤ በላከው መግለጫ ተናግሯል።

ቀደም ብሎ የከተማዋ የታሊባንኖች አዛዥ አራቱን አጥቁዎች ወደ ዩኒቨርስቲው የላክናቸው እኛ ነን ብሎ ነበር። የዜናውን ዘገባ ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

ፓኪስታን በሚገኝ ዩኒቨርስቲ አጥቂዎች ቦምብ አፈንድተው ቢያንስ ሃያ አንድ ሰዎች ገድለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:50 0:00

XS
SM
MD
LG