በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፓኪስታን ድንበር በሚገኝ የህንድ የአየር ክልል ለመቆጣጠር የተጀመረ ጦርነት ዛሬም ቀጥሏል

ወታደራዊ ባለሥልጣናት በሰጡት ቃል ቢያንስ ሁለት ታጣቂዎች በአንድ ህንፃ ውስጥ ተጣብቀውና መውጫ አጥው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ፓኪስታን ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የህንድ የአየር ክልል ለመቆጣጠር የተጀመረው ጦርነት ዛሬ ሰኞ 3ኛ ቀኑን ይዟል።

ወታደራዊ ባለሥልጣናት በሰጡት ቃል ቢያንስ ሁለት ታጣቂዎች በአንድ ህንፃ ውስጥ ተጣብቀውና መውጫ አጥው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ሌሎች ባለሥጣናት በበኩላቸው፣ ወደ 7 የሚሆኑ ወታደሮችና 4 ታጣቂዎች፣ ፓታንኮት(Pathankot) አየር ክልል ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ ማለዳ ላይ በተካሄደው ጥቃት መገደላቸውን አመልክተዋል።

አንድ ወታደራዊ መኰንን በሰጠው ቃል እንደገለጸው፣ አጥቂዎቹ ከባድ ጦር መሣራያ በመያዝ በቂ ዝግጅት አድርገው ነበር ብሏል። የዜና ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ፓኪስታን ድንበር በሚገኝ የህንድ የአየር ክልል ለመቆጣጠር የተጀመረ ጦርነት ዛሬም ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:44 0:00

XS
SM
MD
LG