ዋሺንግተን ዲሲ —
በጊኒ ፕረዚዳንታዊ ምርጫ የተወዳደሩት የተቃውሞ መሪ ሴሉ ዳለይን ዲያሎ፣ የምርጫው ኮሚሽን ስለ ኦፊሴላዊው ውጤት ከማስታወቁ በፊት አሸንፍያለሁ በማለታቸው፣ ሌሊቱን በተነሳው ግጭት፣ ቢያንስ ሦስት ስዎች እንደተገደሉ፣ የሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲ ገልጿል።
የዲያሎ አሸንፊያለሁ ማለት፣ ከተወዳደሪያቸው ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ጋር፣ የፍጥጫ ሁኔታ አሰከትሏል። ለአስርተ ዓመት ያህል ሥልጣን ላይ የቆዩት ኮንዴ፣ ለሦስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ሲሉ፣ የሁለት ዓመታት የጊዜ ገደብ ያስቀመጠውን ህገ መንግሥት ለውጠው ለውድድር በመቅረባቸው፣ ተቃዋሚውን ወገን አስቆጥቷል።
ምርጫ ከመካሄዱ በፊትም ቢሆን፣ የምርጫው ውጤት በሚያስከትለው ጠብ ምክንያት፣ በምዕራብ አፍሪካይቱ ሀገር፣ የዘር ግጭት ሊነሳ እንደሚችል፣ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ሲናገሩ ቆይተዋል።
የ13፣ የ14 እና የ18 ዓመት እድሜ ልጆችና አንድ ወጣት የተገደሉት፣ ትናንት ማታ ተቃዋሚው ፓርቲ የድል በዓል ሲያደርግ፣ የፀጥታ ሃይሎች በዓሉን ለማስቆም በወሰዱት እርምጃ ነው ሲል፣ የጊኒ ዲሞክራስያዊ ኃይሎች የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ፣ ዛሬ ንጋት ላይ ገልጿል።