በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጊኒ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የድምጽ ቆጠራ


ጊኒ ውስጥ በተካሄደው ምርጫ አሸናፊውን ለማወቅ፣ የምርጫው ድምጽ እየተቆጠረ
ጊኒ ውስጥ በተካሄደው ምርጫ አሸናፊውን ለማወቅ፣ የምርጫው ድምጽ እየተቆጠረ

ጊኒ ውስጥ በተካሄደው ምርጫ አሸናፊውን ለማወቅ፣ የምርጫው ድምጽ እየተቆጠረ ነው።

የርዕሰ-ብሄርነት ጊዜው በሁለት ዓመታት ብቻ እንዲወሰን የሚያዘው የሀገሪቱ ህገ መንግሥት፣ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ለሦስተኛ ጊዜ እንዲወዳደሩ በሚያስችል መንገድ በመሻሻሉ፣ ለወራት ያህል ተቃውሞ ሲካሄድ ቆይቷል።

ኮንዴ ለአስርተ-ዓመታት ያህል በተቃዋሚነት ሲንቀስቀሱ ከቆዩ በኋላ፣ ከ10 ዓመታት በፊት በተመረጡበት ወቅት፣ በሃገሪቱ የመጀመርያው በዲሞክራስያዊ መንገድ የተመረጡ መሪ ሆነዋል።

ባለፈው ዓመት በአዲሱ ህገ-መንግሥት ላይ ህዝባዊ ተቃውሞ በተነሳበት ወቅት፣ ቢያንስ 50 ሰዎች እንደተገድሉ ታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዥ፣ በሀገሪቱ የሚመለከታቸው ክፍሎች ሁሉ፣ የምርጫው ሂደት በአካታችነትና በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ እንዲጥሩ ጥሪ አድረገዋል።

ጉተሬዥ አያያዘውም፣ ሁሉም የፖለቲካ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው፣ ከማነሳስት ተግባር፣ አቀጣጣይ ቋንቋን ከመጠቀም፣ ከዘር ለይነትና ግጭት ከማስነሳት እንዲቆጠቡ ተማጽነዋል። የሚያከራክር ሁኔታ ከተፈጠረም፣ በህጋዊ መንገድ እንዲፈታ ዋናው ፀሃፊው መክረዋል።

XS
SM
MD
LG