በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጊኒ ፕረዚዳንታዊ ምርጫ


የጊኒ ምርጫ
የጊኒ ምርጫ

ጊኒ ውስጥ ፕረዚዳንት አልፋ ኮንዴ ለሶስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩበት ፕረዚዳንታዊ ምርጫ ዛሬ ሲካሄድ ውሏል።

የጊኒ ህዝባዊ ስብስብ ፓርቲ አባል የሆኑት ኮንዴ ሀገሪቱ እአአ በ1958 አም ከፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ የመጀመርያው በዲሞክራስያዊ መንገድ የተመረጡ ፕረዚዳንት ነበሩ። ስልጣን ላይ የወጡት ከ 10 አመታት በፊት ነው።

ኮንዴን የሚወዳደሩት በአምባገነኑ መሪ ላንሳና ኮንቴ ስር ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሴሉ ድለይን ዶያሎ ናቸው።

ፕረዚዳንት ኮንዴ ባለፈው መጋቢት ወር በህገ መንግስቱ ለውጥ አድርገው ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር የወሰኑት ሀገሪቱን አዘምናለሁ በማለት ነው። ነገር ግን በሁለት የስልጣን ጊዜ ብቻ የሚወስነውን ህገ-መንግስት ለሶስተኛ ጊዜ እንዲወዳደሩ በሚያስችላቸው መንገድ ለውጠው ለመወዳደር መወሰናቸው በመላ ሀገሪቱ ተቃውሞ ማስነሳቱ አልቀረም።

አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ቡድኖች ደግሞ የ82 አመት እድሜው ፕረዚዳንት ወደ ፍጹማዊ አገዛዝ እያመሩ ሳይሆን አይቀርም እያሉ ነው።

XS
SM
MD
LG