በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ ሰርጥ ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ አሰቃቂ ነው ተባለ


በጋዛ አል አህሊ አራብ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል በተፈጸመ የሮኬት ጥቃት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን የተገደሉበት ሆስፒታል አካባቢ ንብረቶቿን ይዛ የምትሄድ ታዳጊ እአአ ጥቅምት 18/2023
በጋዛ አል አህሊ አራብ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል በተፈጸመ የሮኬት ጥቃት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን የተገደሉበት ሆስፒታል አካባቢ ንብረቶቿን ይዛ የምትሄድ ታዳጊ እአአ ጥቅምት 18/2023

ላለፉት 11 ቀናት በጋዛ ላይ የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት፣ በትምህርት ቤቶች እና በሆስፒታሎች ላይ መጠነ ሰፊ ውድመት አስከትሏል። አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችንም አፈናቅሏል። ከፍተኛ የሆነ የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት እንደሚኖር የረድኤት ድርጅቶች በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው።

ከሳምንት በፊት ሐማስ ያደረሰውን ድንገተኛ ጥቃትን ተከትሉ፣ እስራኤል ሰዎች ተጨናንቀው የሚኖሩባት ጋዛ ላይ የማያቋርጥ የአየር ድብደባ ፈጽማለች፡፡

የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል እና የቀይ ጨረቃ ማኅበረሰብ ቃል አቀባይ የሆኑት ቶማሶ ዴላ ሎንጋ፣ በጋዛ የሚገኙት የማኅበረሰቡ አባላት መድሓኒት እና ነዳጅ እያለቀባቸው መሆኑን ተናግረዋል። ቀይ መስቀል በጋዛ ሰርጥ ሁለት ሆስፒታሎች እንዳሉት የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ ሆስፒታሎቹ በነዳጅ የሚሠሩ በመሆኑ፣ ነዳጅ የማይኖር ከሆነ፣ ኤሌክትሪክም ስለማይኖር ለመሥራት እንደሚቸገሩ አስታውቀዋል።

ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ፣ 400መቶ ሺሕ የሚሆኑ ፍልስጤማውያን ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ተገደዋል። በጋዛ ሰርጥ እና በእስራኤል መካከል ያለውን መተላለፊያ እስራኤል ላልተወሰነ ግዜ ዘግታለች፡፡ ከአምስት ቀናት በፊት፣ የቦምብ ጥቃት እንደሚኖር በማስጠንቀቅ፣ ነዋሪዎች ወደ ደቡብ የጋዛ ሰርጥ ክፍል እንዲዛወሩ እስራኤል አስታውቃ ነበር።

በሰዎች ዘንድ ተስፋ መቁረጥ እንደሚታይ የገለጹት የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል እና የቀይ ጨረቃ ማኅበረሰብ ቃል አቀባይ፣ በጋዛ የሚገኘው የቀይ ጨረቃ ሆስፒታል ሠራተኞች ለቀው እንዲወጡ ሶስት ግዜ ተጠይቀው እንደነበርና፣ ሠራተኞቹ ግን ታካሚዎችን ማስወጣት እንደማይችሉ ገልጸው ለመቆየት ወስንዋል ብለዋል።

በሺሕ የሚቆጠሩ ፍልስተኞች በጋዛ እና በግብጽ መካከል ባለው ድንበር ላይ ተሰባስበዋል። ግብጽ ጥበቃዋን በማጠናከር፣ ፍልሰተኞቹ አልፈው እንዳይገቡ ከልክላለች ሲል ጀሩሳሌም ፖስት ጋዜጣ ዘግቧል።

“እስራኤል እና አሜሪካ፤ ግብጽ ፍልስጤማውያኑን እንድትቀበል እና የሌሎች ሀገራት ዜጎችንም እንድታስገባ ጠይቀዋል። የውጪ ዜጎቹ በእስራኤል ወይም በፍልስጤም አስተዳደር በኩል አስፈላጊውን የጉዞ ሰነድ ካሟሉ እንደምትፈቅድ፤ይህም የሚሆነው፣ የስብዓዊ ርዳታ ቀድሞ የሚገባ ከሆነ እንደሆነ ማስታወቋን እና ፍልስጤማውያኑን በተመለከተ ግን፣ አንድ ግዜ ለቀው ከወጡ ተመልሰው ወደ ጋዛ እንዲገቡ ስለማይፈቀድላቸው እንደማታስገባ ግብጽ መግለጿን የመካከለኛው ምሥራቅ ተቋም ዓባል የሆኑት ሚሬት ማብሩክ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ፍልስጤማውያን ወደ ግብጽ ድንበር እያመሩ መሆኑን በቅርብ ምሥራቅ የተመድ የርዳታ እና የሥራ ድርጅት ድርጅት አታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG