በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን እስራኤል ናቸው


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቴል አቪቭ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቴል አቪቭ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ረቡዕ እስራኤል ገብተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋራ ተነጋግረዋል። ባይደን ወደ እስራኤል የተጓዙት በጋዛ ሆስፒታል ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ ከደረሰ እና ጥቃቱን ተከትሎ በቀጠናው ከፍተኛ ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ በኋላ ነው።
ባይደን በእስራኤል፣ ቴል አቪቭ ከተማ ተገኝተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ፣ በጋዛ ሆስፒታል ላይ ስለተፈፀመው የቦምብ ጥቃት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
"ትላንት በጋዛ ሆስፒታል ላይ በደረሰው ፍንዳታ እጅግ አዝኛለሁ፣ ተናድጃለሁ። አሁን ባየሁት መሰረት ግን ጥቃቱ በእናንተ ሳይሆን በሌላው ቡድን የተፈፀመ ይመስላል። ነገር ግን ብዙ እርግጠኛ ያልሆኑ ሰዎች አሉ። ስለዚህ ብዙ ነገሮችን ማለፍ መቻል አለብን።" ብለዋል።
ባይደን የረጅም ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስ አጋር ለሆነችው ሀገር ድጋፋቸውን ለማሳየት ከእስራኤል መሪዎች ጋራ ስብስባ እያደረጉ ባሉበት ወቅት፣ የአረብ መሪዎች በዮርዳኖስ ሊያደርጉት የነበረው ሌላ ቁልፍ ስብሰባ፣ በቦምብ ጥቃቱ ምክንያት ተሰርዟል።
የሐማስ ታጣቂዎች፣ በጋዛ ከተማ አህሊ አረብ ሆስፒታል ላይ ለደረሰው ፍንዳታ እስራኤልን ተጠያቂ ሲያደርጉ፣ የእስራኤል መከላከያ ኃይሎች በበኩላቸው፣ የፍልስጤም መደበኛ ያልሆነ ጦር የተኮሰው ሚሳይል መስመሩን ስቶ ሆፒታሉን እንደመታ በመግለፅ፣ የደረሰባቸውን ክስ ተቃውመዋል። ታጣቂው ቡድንም ለጥቃቱ ሀላፊነት አልወሰደም።
ባይደን በቴል አቪቭ የሚያደርጉትን ጉብኝት ሲጨርሱ፣ ወደ ዮርዳኖስ ዋና ከተማ፣ አማን እንዲያቀኑ ቀጠሮ ተይዞላቸው ነበር። ሆኖም በጋዛ ሆስፒታል ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ፣ የእስራኤል ጎረቤት ሀገራት መሪዎች - የዮርዳኖስ ንጉስ አብዱላህ እና የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል-ሲሲ- ከባይደን እና ከፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ጋር ስብሰባውን ላለማካሄድ በመወሰናቸው፣ ጉዟቸው ተሰርዟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG