ዋሽንግተን —
በአሁኑ ሰዓትም ዘመድ ያለው በየዘመድ አዝማዱና ጓደኛው ቤት እየተጠለለ መሆኑን ገልጸው መጠጊያ የሌላቸው ሰዎች ግን ውጭ ሜዳ ላይ እና ጎርፉ ባለበት አካባቢ ለማደር መገደዳቸውን ይገልፃሉ።
በአሁኑ ሰዓትም በቂ እርዳታ እየተሰጣቸው እንዳልሆነ ጠቁመው ቀድሞውኑ በከተማው በቂ የጎርፍ ማስተላለፊያ ቱቦ ቢሠራ ኖሮ ከእንዲህ ያለ አደጋ ሊተርፉ ይችሉ እንደነበር አስረድተዋል።
የአዳማ ከተማ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀቢብ ቃሲም ስለጉዳዩ ተጠይቀው አደጋው በተፈጠሮ የመጣ እንደሆን ገልፀው፤ በአሁኑ ሰዓት የተፈናቀሉትን 4,500 ሰዎች ለመርዳት ሦስት የመርጃ ጣቢያዎች አቋቁመው እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የዘጠኝ ወር ነፍሰጡር መሆኗን የገለፀችልን ወ/ሮ ቢሊሱማ ሁሴን ቤቷ በጎርፉ በመጠረጉና መጠለያ ባለማግኘቷ ዛፍ ስር ማደሯን ተናግራለች።
በዚህ ጎርፍ ሁለት የጎዳና ተዳዳሪዎች መወሰዳቸውን ነዋሪዎችን ጠቅሰን በትናንትናው ዕለት መዘገባችን ይታወሳል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።