በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሃገር ማስተላለፍ ወይም ዘመናዊ ባርነት


ከማልታዋ ዋና ከተማ ቫሌታ ሆስፒታል አንዲት ሴት የባለቤታቸውን ስከሬን በሚረከቡበት ጊዜ በዋይታ ሃዘናቸውን እየገለጹ። ባለቤታቸው በሕገ-ወጥ መንገድ ከሊብያ ወደ አውሮፓ በሚጓዙበት ወቅት መርከብ ሰምጣ ነው ህይወታቸውን ያጡት። ( እአአ 2011 ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS)
ከማልታዋ ዋና ከተማ ቫሌታ ሆስፒታል አንዲት ሴት የባለቤታቸውን ስከሬን በሚረከቡበት ጊዜ በዋይታ ሃዘናቸውን እየገለጹ። ባለቤታቸው በሕገ-ወጥ መንገድ ከሊብያ ወደ አውሮፓ በሚጓዙበት ወቅት መርከብ ሰምጣ ነው ህይወታቸውን ያጡት። ( እአአ 2011 ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS)

ዛሬ በዓለማችን ከ 20 ሚሊዮን በላይ የዚህ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሃገር ማስተላለፍ ወይም ዘመናዊ ባርነት ሰለባዎች አሉ ይልና የቪኦኤ ርዕሰ አንቀጽ ሃተታውን ይቀጥላል።

ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሃገር ማስተላለፍ ወይም ዘመናዊ ባርነት፥ በዓለም ዙሪያ በብዙ ቢሊዮን ዶላር የሚካሄድ እንቅስቃሴ ነው። ይህ ሕገ-ወጥ ተግባር መንግሥታትን ያኮሰምናል፥ የሃገሮች ብልጽግና ፀር የሆነውን ሙስናን ያለመልማል። ድርጊቱ እንደ ሱስ አስመጪ ንግድና የጦር መሣሪያን በድብቅ የማስተላለፍ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ያጠናክራል። አሸባሪዎች እንቅስቃሴዎቻቸውን በገንዘብ የሚያግዙበት አንደኛው መንገድም ነው። ዛሬ በዓለማችን ከ 20 ሚሊዮን በላይ የዚህ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሃገር ማስተላለፍ ወይም ዘመናዊ ባርነት ሰለባዎች አሉ ይልና የቪኦኤ ርዕሰ አንቀጽ ሃተታውን ይቀጥላል።

ባሁኑ ወቅት በዓለማችን አንድም ሀገር ከዚህ ሰብዓዊ መቅሰፍት ሊያመልጥ አይችልም። ዩናይትድ ስቴትስን ብንወስድ፥ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሀገር የሚተላለፉ ሰዎችና ባስገዳጅ ሥራ የሚመረቱ ቁሳቁሶች በብዛት የሚገቡባባት ሆና እናገኛለን። ይህም ማለት፥ ይህን የሰው ልጆች መቅሰፍት የምንዋጋ ከሆነ፥ ከራሣችን መጀመር አለብን ሲልም ያሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ በርዕሰ አነጹ አስገንዝቧል።

ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ፥ ዘመናዊ ባርነትን በመዋጋቱ ተግባር የዩናይትድ ስቴትስን መግሥትን ምላሽ ለማጠናከርና ለማስተባበር ከሦስት ዓመታት በፊት በርካታ እርምጃዎችን ወስደዋል። በወቅቱ ትኩረት የሰጧቸውም አራት የስልት ዘርፎች -

ከሕግ አንጻር - ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሃገር የሚያስተላልፉ ሰዎች እነማን እንደሆኑ መከታተል፥ በድርጊቱ መሳተፋቸው የተረጋገጠባቸውን እየያዙ በቁጥጥር ሥር ማዋልና ለፍርድ ማቅረብ አንደኛው ሲሆን፥ ለድርጊቱ ሰለባዎች የጤና አገልግሎት መስጠት፥ የሕጻናትን ጤና መንከባከብ የሚለው ደግሞ ሁለተኛው ነው። በንግድ መልክ ሰዎቹ በሚተላለፉባቸው መንገዶች የትም ቦታ ላይ አስገዳጅ ሥራ አለመፈጸሙንና የሚመረቱት ቁሳቁሶች በዩናይትድ ስቴትስ ገበያ ላይ አለመዋላቸውን ማረጋገጥ ሦስተኛው እርምጃ ሲሆን የችግሮቹን ክብደት ሕዝብ እንዲረዳ ማድረግ እንዲሁም የዚህን የዘመናዊ ባርነት ሰለባዎች መለየት የሚያስችሉ ሥልጠናዎችን ለመንግሥት መሥጠትና ባጠቃላይ ሕዝቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ ማድረግ የሚሉ ናቸው። ፕሬዘዳንቱ ይህን የያዝነውን ያውሮፓውያኑን ወር ጥር (January) በያመቱ ብሄራዊ የዘመናዊ ባርነትና ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሃገር ማስተላለፍን የምንከላከልበት ወር እንዲሆን አውጀዋል።

”የደህንነት ጥበቃ አባሎቻችን፥ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሃገር የሚያስተላልፉ መረቦችን ለመለየት የሚያስችላቸው በቂ ሃይል መድበዋል። ሕግ አስከባሪ መኮንኖችም መረቦቹን ለመበጣጠስ ተንቀሳቅሰዋል። የወንጀለኛ መረቡን መሪዎች ለፍርድ አቅርበው ለማስቀጣት ደግሞ ዓቃብየነ ሕግ ያላሰለሰ ጥረት ይዘዋል” ብለዋል ፕሬዘዳንት ኦባማ በዘንድሮው የጥር (January) ዘመቻ መልዕክታቸው ሲናገሩ።

በመጨረሻም፥ እኛ እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች በሕገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሃገር መተላለፋቸውን ለማስወገድ እየታገልን ባለንበት ወቅት፥ ድርጊቱን ከመላው ዓለም ለማጥፋት የተያዘውን ጥረት ደግሞ መምራታችንን እንቀጥላለን ሲሉ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የተናገሩትን ጠቀሦ የቪኦኤ ርዕሰ አንቀጽ ሃተታውን ደምድሟል። የቪኦኤ ርዕሰ አንቀጹን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሃገር ማስተላለፍ ወይም ዘመናዊ ባርነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:45 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG