አዲስ አበባ —
አፍሪቃ በሚያጋጥሟት የጸጥታ ችግር ላይ የሚወያየዉ የጣና ፎረም ያመነጫቸዉ የመፍትሔ ሃሳቦች አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን አማካሪ ቦርዱ አስታዉቀቅዋል።
የጣና ፎረም አማካሪ ቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እንዳሉት፣ አገሮች የሚመነጩትን ሃሳቦች እየተጠቀሙባቸዉ ነዉ።
አምስተኛዉ የጣና ፎረም ስብሰባም ከአንድ ወር በኋላ በባህር ዳር ይካሄዳል።
እስክንድር ፍሬዉ ዝርዝሩን ዘግቧል።
ለዝርዝሩ የድምጽ ፋይሉን በመጫን የእስክንድር ፍሬዉን ዘገባ ያድምጡ።