አዲስ አበባ —
በካርቱም የተሰባሰቡት የኢትዮጵያ፥ የግብፅና የሱዳን የውጭ ጉዳይና የውሃ ሃብት ሚኒስትሮች፥ በሕዳሴው ግድብ ላይ ጥናት የሚያካሂዱ ኩባንያዎችን መርጠው አጠናቀዋል። የቴክኒክ ጥናቱ የፊታችን ጥር መጨረሻ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
እስክንድር ፍሬው ተከታዩን አጠናቅሮ የላከውን ዘገባ ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።