በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዲሲ የሚቀመጡ ኢትዮጵያውያን በሥራ ቦታ ላይ ሊኖር ይገባል ባሉት የመብትና የነፃነት ጥያቄ ዙሪያ ስብሰባ አካሄዱ


በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በተለይም ቨርጂንያ ውስጥ በሚገኘው ሬገን አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ ባሉ ልዩ ልዩ ኩባንያዎች ተቀጥተው የሚገኙ ሠራተኞች በትናንቱ ዕለት እዚያው አውሮፕላን ጣቢያው በሚገኝ አዳራሽ አንድ ታላቅ ስብሰባ አድርገው ነበር። ስብሰባው በሥራ ቦታ ሊኖር ይገባል ባሉት የመብትና የነፃነት ጥቄን ዙሪያ ያጠነጠነ ነበር።

በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በተለይም ቨርጂንያ ውስጥ በሚገኘው ሬገን አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ ባሉ ልዩ ልዩ ኩባንያዎች ተቀጥተው የሚገኙ ሠራተኞች በትናንቱ ዕለት እዚያው አውሮፕላን ጣቢያው በሚገኝ አዳራሽ አንድ ታላቅ ስብሰባ አድርገው ነበር።

ስብሰባው በሥራ ቦታ ሊኖር ይገባል ባሉት የመብትና የነፃነት ጥቄን ዙሪያ ያጠነጠነ ነበር። ሠራተኞቹ ባብዛኛው አፍሪቃውያን ስደተኞች ናቸው። ከሌላው ክፍለ-ዓለም እንደ ላቲን አማሪካ ከመሳሰሉ አገሮች የሆኑም አሉ። ከጠቅላላው ከነዚህም የሚበዙቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የ"ይቻላል!" መፈክር እያሰሙ ነው ወደ ስብሰባው ያመሩት። "ማሸነፍ ይቻላል! ሲ-ሴይ-ፖይዴ" እያሉ ወደ ስብሰባው አዳራሽ ሲገቡ፣ አዳራሹ ምንጣፍ ተጎዝጉዞለት፣ ቁርሱ ቀርቦለት የተዘጋጀው ስኒና ረከቦት ነበር።

የጥሪያቸው ወረቀትም "ቡና ለፍትህ" ይላል። ይህን የመብት ማስከበሪያ ስብሰባቸውን ግን፣ ለምን ይሆን "ቡና ለፍትህ" በሚል ኃይለ-ቃል ያጀቡት? ብለን ስንጠይቅ፣ እንግዳ ለማስቀደም መሆኑንም ተረድተናል።

አቶ በኃይሉ ወልደዮሃንስ ለአፍሪካ ማኅበረሰብ (African Communities Together)ተሟጋች ወይም የውክልና ሥራ ነው የሚሰሩት። በስብሰባው ውስጥ ያላቸውን ሚና፣ ማን እንዳዘጋጀው፣ ዓላማውን፣ እና ምን ውጤት እንደሚጠበቅ ሰፋ ያለ መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህ ዓይነቱ የመብት ማስከበር እንቅስቃሴ፣ የየማኅበረሰቡ ተቋማት መጋበዝ አለባቸው ብሎ ያምናል። እናም ለስብሰባው በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ማኅበራት ተወካዮች፣ የመገናኛ አውታር (ሚዲያ) ሠራተኞች፣ የልዩ ልዩ የንግድ ባለቤቶች፣ የልዩ ልዩ ሃይማኖት መሪዎች፣ የሲቪክ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ ተቋማት ተወካዮች የተጋበዙ መሆናቸውን አቶ በኃይሉ ገልጸዋል።

በስርፋው የነበረው ባልደረባችን አዲሱ አበበ ያጠናቀረውን ዝርዝር ለማዳመጥ፣ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያድምጡ።

በዲሲ የሚቀመጡ ኢትዮጵያውያን በሥራ ቦታ ላይ ሊኖር ይገባል ባሉት የመብትና የነፃነት ጥያቄ ዙሪያ ስብሰባ አካሄዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:41 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG