በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሴቶች እና የፖለቲካ ተሳትፏቸው


ሴቶች እና የፖለቲካ ተሳትፏቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:02 0:00

ሴቶች እና የፖለቲካ ተሳትፏቸው

በወቅታዊው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ክዋኔ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ እየቀነሰ እንደመጣ፣ በዘርፉ የተሰማሩ ሦስት የሴቶች እና የሰብአዊ መብቶች ድርጅት መሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡

ሴቶች፣ ከመንግሥታዊ ተቋማት እና ከውሳኔ ሰጭነት ዕርከን ውጭ እየሆኑ መምጣታቸው፣ የሴቶችን መብቶች ለማስከበር አዳጋች እንደሚያደርገው ተሟጋች ድርጅቶቹ አመልክተዋል፡፡

ሴቶች በተለይ ታላላቅ እና እጅግ ወሳኝ በሆኑ የአገሪቱ ጉዳዮች ውስጥ እየተሳተፉ እንዳልኾነ የጠቀሱት መሪዎቹ፣ በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ግጭቶች ግንባር ቀደም ተጠቂዎች ቢኾኑም፣ ችግሮቹን ለመፍታት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ግን አለመካተታቸውን ተናግረዋል፡፡ በማሳያነትም፣ ለፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት በተደረገው ድርድር ውስጥ አንዲትም ኢትዮጵያዊት ሴት አለመሳተፏን በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ጉዳይ ጋራ በተያያዘ፣ የሴታዊት ንቅናቄ መሥራች እና አስተባባሪ ዶክተር ስኂን ተፈራ፣ የ“ትምራን” አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋም ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ኢየሩሳሌም ሰሎሞን፣ “ስብስብ ለሰብአዊ መብት በኢትዮጵያ” ዲሬክተር ወ/ት መሠረት ዓሊን አነጋግረናል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG