በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለኢትዮጵያውያት ሴቶች የነጻነትና እኩልነት ትግል ታሪክ


ለኢትዮጵያውያት ሴቶች የነጻነትና እኩልነት ትግል ታሪክ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:55 0:00

ለኢትዮጵያውያት ሴቶች የነጻነትና እኩልነት ትግል ታሪክ

ኢትዮጵያውያት ሴቶች ለነጻነት እና እኩልነት ያደረጓቸው የትግል ታሪኮች፣ “በቂ ትኩረት አልተሰጣቸውም፤” ሲሉ የታሪክ ተመራማሪዎች ተናገሩ።

የባህል እና ታሪክ ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር አሕመድ ዘካርያ፣ ኢትዮጵያውያት ሴቶች ካለባቸው ማኅበራዊ ኃላፊነት ባሻገር፣ በአገሪቱ የታሪክ ሒደቶች ውስጥ ከፖለቲካዊ ትግል ተሳትፎ እስከ አመራር ሰጭነት ሚና እንደነበራቸው ያወሳሉ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቋም የማኅበረሰብ ታሪክ አጥኚው ዶክተር ነጻነት ገብረ ሚካኤል በበኩላቸው፣ ለራሳቸው መብቶች መከበርም ሆነ ለማኅበረሰባዊ ለውጥ ያበረከቱት ሚና በታሪክ ንግሮቻችን ላይ ጎልቶ እንዳልታየ ይናገራሉ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም፣ በተማሪዎች ንቅናቄ ወቅት ሴቶች የነበራቸውን ሚና የሚዳስሱ የጥናት እና ምርምር ሥራዎችን በማሳተም ክፍተቱን ለመሙላት እየሠራ እንደሚገኝም አጥኚው ይጠቁማሉ። በዚህ ዙሪያ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG