ዋሽንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምሕርት መግቢያ ፈተና መንግሥት የማኅበራዊ መገናኛ ድረ ገፆችን ከዘጋ በኋላ ተጀምሯል። እየተናፈሱ ያሉ ውዥንብሮችን ለመግታት ሲባል የማኅበራዊ ድረ-ገፆች እንዲዘጉ መወሰኑን መንግሥት አስታውቋል። እርምጃው በተጠቃሚው ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል። አንዳንድ ተማሪዎች ግን በአዎንታዊ ጎኑ ተመልክተውታል።
መንግሥት ለምንም ዓላማ ድረግጽ ምዝጋቱን በይፋ ሲናገር የመጀምሪያው ነው። ማኅበራዊ ድረ ገፆች አለመሥራት ያማረራቸው በርካታ ተገልጋዮችም ቅሬታቸውን ሲያንጸባርቁ ተስተውሏል።
እስክንድር ፍሬው ተከታዩን ዘገባ ልኳል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።