በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የቴሌቭዥን ድራማዎች የታሪክ ጭብጥና የገጸ ባሕሪያት አሳሳል ትውልድን አምካኝ ናቸው” ባለሞያዎች


ቴዎድሮስ ጸጋዬ፣ዳዊት ተስፋዬ እና በላይነህ አቡኔ
ቴዎድሮስ ጸጋዬ፣ዳዊት ተስፋዬ እና በላይነህ አቡኔ

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና በኢቢኤስ ቴሌቭዠን ጣቢያዎች ላይ ከዘጠኝ በላይ ተከታታይ የቴሌቭዠን ፕሮግራሞች በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ድራማዎቹ በከፍተኛ ሁኔታ አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል እይታ የተቆጣጠሩ ናቸው፡፡ በእነዚህ በብዛት እየቀርቡ ባሉ የቴሌቭዥን ድራማዎች የታሪክ ጭብጥና የገጸ ባሕሪያት አሳሳል ለትውልድ የሚተላለፈው መልዕክት ምንድነው? በሚል መጠይቅ የሚንደረደረው የዛሬው የትንታኔ ፕሮግራም ባለሞያዎችን አካቶ ይዟል፡፡አዘጋጇ ጽዮን ግርማ ነች፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቭዠን ጣቢያዎች ላይ ከዘጠኝ በላይ ተከታታይ የቴሌቭዠን ፕሮግራሞች በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ድራማዎች ከፍተኛ ተመልካች ያላቸውና አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል እይታ የተቆጣጠሩ ናቸው፡፡ በእነዚህ በብዛት እየቀርቡ ባሉ የቴሌቭዥን ድራማዎች የታሪክ ጭብጥና የገጸ ባሕሪ አሳሳል ለትውልድ የሚተላለፈው መልዕክት ምንድነው? በሚል መጠይቅ የዛሬው ትንታኔ ይንደረደራል፡፡

ቴዎድሮስ ጸጋዬ ይባላል፡፡ የሕግ ትምሕርት ተመራቂ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት የጣዕም ልኬት እና ርዮት በተሰኙ የሬዲዮ ፕሮግራሙ ላይ ያነሳቸው በነበሩ ሞጋች ሐሳቦች ይታወቃል፡፡ እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ከመጣም በኋላ በኢቢኤሰ ቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ ፕሮግራም ያዘጋጃል፡፡ የቴሌቭዠን ድራማዎቹ የሚያነሱት ሐሳብ፣ የሚቀርጿቸው ገጸ ባሕሪያትና የታሪክ አወቃቀር እንዲሁም የገጸባህሪ አሳሳል አዳዲስ የክፋት ሐሳቦችን የሚያስተዋውቁ ናቸው ይላል፡፡

Ethiopian Movies posters
Ethiopian Movies posters

ዳዊት ተስፋዬ የቲያትርና ኪነጥበብ ትምሕርት ተመራቂ ነው፡፡ ፊልም ጸሐፊ ፣ዳሬይሬክተርና ፕሮዲዩሰር ነው፡፡ ትዝታዬ የሚካኤል በላይነህ፣እርጅና መጣና የሃይሌ ሩትስ የሙዚቃ ክፖችን ዳይሬክት አድርጓል፡፡ዳና የተሰኘ ተከታታይ ሬዲዮ ድራማ የተወሰነ ክፍል ዳይሬክት አድጓል፡፡ ዘጠኘ ሞት የተሰኘ ፊልም ደራሲ ዳይሬክተርም ነው፡፡ የቴሌቭዠን ድራማዎች እውቀት በሌላቸው ሰዎች መሠራታቸው የተበላሸ ውጤት ለማየት አሰችሎናል ይላል፡፡

በላይነህ አቡኔ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቲያትር እና ሥነ ጥበባት ትምሕርት ክፍል ከ30 ዓመት በላይ አስተምሯል፡፡ ጸሐፊም ነው፡፡ አሁን ለእረፍት እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ይገኛል፡፡ የቴሌቭዥን ድራማዎች ትውልድን ለመቅረጽ ከፍተኛ ድርሻ ስላላቸው በጥናት ላይ ተመስርቶ በጥንቃቄ ሊሠሩ ይገባል ይላል፡፡ ሁሉም በዚህ ዘገባ ተካተዋል፡፡ ዘገባው የሠራችው ጸዮን ግርማ ነች፡፡

ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

“የቴሌቭዥን ድራማዎች የታሪክ ጭብጥና የገጸ ባሕሪያት አሳሳል ትውልድን አምካኝ ናቸው” ባለሞያዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:37 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG