በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ጦር ኤል ቡርን ለቅቆ ወጣ


ሶማሊያ
ሶማሊያ

ማዕከላዊ ሶማሊያ ውስጥ ቁልፍ የሚባል ወታደራዊ መደብ ይዞ የቆየው የኢትዮጵያ ጦር ያለአንዳች የቅድሚያ ማስታወሻ አካባቢውን ጥሎ መውጣቱን የኤል ቡር ከተማ ነዋሪዎችና የከተማዪቱ አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጦር ኤል ቡርን ለቅቆ መውጣትን ተከትሎ በከባድ የታጠቁ የአማፂው ቡድን አል ሻባብ ተዋጊዎች ያለ አንዳች መሰናክል ዛሬ ማለዳ ላይ ከተማዪቱን መቆጣጠራቸው ተነግሯል፡፡

«ኢትዮጵያዊያኑ ከኤል ቡር የወጡበትን ምክንያትም ሆነ እንደሚወጡ ቀድመው ሳይነግሩን ያየናቸው መደቡን ለቅቀው ሲወጡ ብቻ ነው፤ እነርሱን ተከትለው የእኛም ወታደሮች ወጥተዋል» ብለዋል አስተዳዳሪው ኑር ሃሰን ጉታሌ፡፡

ወታደሮቹ እንደወጡ የአል ሻባብ ታጣቂዎች ፀረ አይሮፕላን መሣሪያ እላያቸው ላይ በደገኑ ስድስት ፒክ አፕ ተሽከርካሪዎች ሆነው ዛሬ ማለዳ ላይ ወደ ከተማዪቱ ገብተው ተቆጣጥረዋታል፡፡

ሞቃዲሾ የሚገኙት በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሣደር ጃማሉዲን ሙስጠፋ ኦማር ማምሻውን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የኢትዮጵያዊያኑን ወታደሮች ከኤል ቡር መውጣት አረጋግጠው ቀድመው ሳያሳውቁ ወጡ የተባለውን ግን አስተባብለዋል፡፡

ለተጨማሪ ዘገባና ከአምባሣደር ጃማሉዲን ሙስጣፋ ጋር የተደረገውን ቃለ-ምልልስ የያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

የኢትዮጵያ ጦር ኤል ቡርን ለቅቆ ወጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:28 0:00
በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሣደር ጃማሉዲን ሙስጠፋ ኦማር ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:25 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG