No media source currently available
ማዕከላዊ ሶማሊያ ውስጥ ቁልፍ የሚባል ወታደራዊ መደብ ይዞ የቆየው የኢትዮጵያ ጦር ያለአንዳች የቅድሚያ ማስታወሻ አካባቢውን ጥሎ መውጣቱን የኤል ቡር ከተማ ነዋሪዎችና የከተማዪቱ አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡ ሞቃዲሾ የሚገኙት በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሣደር ጃማሉዲን ሙስጠፋ ኦማር ማምሻውን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የኢትዮጵያዊያኑን ወታደሮች ከኤል ቡር መውጣት አረጋግጠው ቀድመው ሳያሳውቁ ወጡ የተባለውን ግን አስተባብለዋል፡፡