በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ጭኖ የመን ይጓዝ የነበረ ጀልባ ተገልብጦ 46ቱ ሞቱ

ቢያንስ አንድ መቶ ፍልሰተኞችን ይዞ ዛሬ ረቡዕ ማለዳ ከሶማሊያ ይጓዝ የነበረ የሕገ ወጥ አሸጋጋሪዎች ጀልባ የመን ሲቃረብ ተገልብጦ አርባ ሥድስት ኢትዮጵያውያን ሰጥመው መሞታቸው እና ሌሎች አሥራ ስድሥት የደረሱበት መጥፋቱ ተገለፀ፡፡

ቢያንስ አንድ መቶ ፍልሰተኞችን ይዞ ዛሬ ረቡዕ ማለዳ ከሶማሊያ ይጓዝ የነበረ የሕገ ወጥ አሸጋጋሪዎች ጀልባ የመን ሲቃረብ ተገልብጦ አርባ ሥድስት ኢትዮጵያውያን ሰጥመው መሞታቸው እና ሌሎች አሥራ ስድሥት የደረሱበት መጥፋቱ ተገለፀ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰት ድርጅት አይኦኤም ከአደጋው የተረፉ ተሳፋሪዎችን ጠቅሶ ሲናገር ጀልባው የመንና ሊሎችም የሰላጤው አገሮች ሥራ ብናገኝ በሚል ተስፋ የተነሱ ሰማኒያ ሦስት ወንዶችና አሥራ ሰባት ፍልሰተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ ነው የመን ሲቃረብ የተገልበጠው።

የአይኦኤም የኦፐሬሽንና የአጣዳፊ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሞሃመድ አብዲኬር ባወጡት መግለጫ በአደን ሰላጤ በፍልሰተኞች ላይ የደረሰው አሳዛኝ አደጋ የሚያሳፍር ነው ብለውታል።

መሃመድ ሼካ የተባሉ የሶማሊያ ቦሳሶ ነዋሪ ከቦሳሱ ከተነሱት ጀልባዎች ባንዱ ላይ ከነብሩትና ሰጥመው ከሞቱት መካከል አስራ አንዱ ሴቶች መሆናቸውን ሰምተናል ብለዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ጭኖ የመን ይጓዝ የነበረ ጀልባ ተገልብጦ 46ቱ ሞቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:57 0:00
ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ጭኖ የመን ይጓዝ የነበረ ጀልባ ተገልብጦ 46ቱ ሞቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:24 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG