በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤንሻንጉል-ጉምዝ የእርሻ ሠራተኞች መጠለፋቸው ተሰማ


አልኑር በሽር ሲባል በቆየ በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል በጉባ ወረዳ በኦሜድላ ቀበሌ ባለ እርሻ ልማት ላይ የሚሠሩ 22 ሠራተኞች በሱዳን ወታደሮች ተጠልፈው መወሰዳቸውን የእርሻ ልማቱ ባለቤት ነኝ ያሉት አቶ ይርሳው የሺወንድም ተናግረዋል።

በቤንሻንጉል-ጉምዝ የእርሻ ሠራተኞች መጠለፋቸው ተሰማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:12 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አልኑር በሽር ሲባል በቆየ በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል በጉባ ወረዳ በኦሜድላ ቀበሌ ባለ እርሻ ልማት ላይ የሚሠሩ 22 ሠራተኞች በሱዳን ወታደሮች ተጠልፈው መወሰዳቸውን የእርሻ ልማቱ ባለቤት ነኝ ያሉት አቶ ይርሳው የሺወንድም ተናግረዋል።

አቶ ይርሳው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ባለፈው ቅዳሜ፤ ሚያዝያ 22 / 2005 ዓ.ም በሁለት ተሽከርካሪዎች የደረሱ የሱዳን ወታደሮች የያዟቸውን ሠራተኞቻቸውን ዲቫዚን የምትባል የሱዳን ከተማ ወይም ቀደም ብላ በምትገኝ ሌላ ስሟን እንደዘነጉ በተናገሯት የሱዳን አነስተኛ ከተማ ውስጥ በእሥር እንደያዟቸው አመልክተዋል።

ሌሎች 18 ሠራተኞች እስከአሁን የት እንዳሉ እንደማያውቁ ገልፀዋል።

የእርሻ ልማቱ “ይርሳው እርሻ ልማት” ወደሚል ስያሜ እየተለወጠ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ይርሳው በግዥ የያዙት ድርጅታቸው ላለፉት አራት ሰሊጥና ጥጥ እንደሚያመርት ገልፀዋል።

የእርሻ ልማቱ ይዞታ ካርታ ያለውና በዚያ መሠረትም ገንዘብ ተበድረበት እየሠሩ ያሉ መሆናቸውን አመልክተው የሱዳን ወታደሮች ባለፈው ዓመትም እንዲሁ ወደ እርሻቸው ዘልቀው የወሰን ድንጋይ እንደተከሉና ሠራተኞችን ለግማሽ ቀን አሥረው እንደለቀቁ አስታውሰዋል።

አሁን ስላለው ሁኔታም ለወረዳውና በአካባቢው ላሉ የፀጥታ ባለሥጣናት አቤት ብለው ምላሽ እየጠበቁ መሆናቸውን አቶ ይርሣው ገልፀዋል።

ለተጨማሪ መግቢያ ላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG