በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማንም አልተረፈም


በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ከቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ የተነሣው ቦይንግ 737 MAX 8 ጄት ተሣፋሪዎች ቤተሰቦች /አዲስ አበባ፤ ዕሁድ፤ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም./
በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ከቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ የተነሣው ቦይንግ 737 MAX 8 ጄት ተሣፋሪዎች ቤተሰቦች /አዲስ አበባ፤ ዕሁድ፤ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም./

ወደ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በየዕለቱ ለሚያደርገው መደበኛ በረራ ዛሬ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ከ38 ደቂቃ ላይ ከቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ ተነስቶ ቢሾፍቱ አቅራቢያ ከተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን በሕይወት የተረፈ ማንም እንደሌለ ተረጋግጧል።

በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ከቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ የተነሣው ቦይንግ 737 MAX 8 ጄት ስባሪ /ከአዲስ አበባ 50 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በምትገኘው ሂጅሬ ቀበሌ - ዕሁድ፤ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም./
በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ከቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ የተነሣው ቦይንግ 737 MAX 8 ጄት ስባሪ /ከአዲስ አበባ 50 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በምትገኘው ሂጅሬ ቀበሌ - ዕሁድ፤ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም./

በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የተመዘገበው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት ጄት 149 መንገደኞችንና ስምንት የበረራ ቡድን አባላትን አሳፍሮ ወደ ናይሮቢ ለመብረር ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ የተነሣው ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ከ38 ደቂቃ ላይ ሲሆን መሬት ከለቀቀ ከስድስት ደቂቃ በኋላ ከምድር መቆጣጠሪያው ጋር የነበረው ግንኙነት መቋረጡ ተገልጿል።

አዲስ አበባ፤ ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ
አዲስ አበባ፤ ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ

ከተሣፋሪዎቹ መካከል ሰላሣ ሁለት ኬንያዊያን፣ ስምንት ካናዳዊያን፣ ስምንቱን የበረራ ቡድኑን አባላት ሳይጨምር ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያንና ስምንት አሜሪካዊያን መንገደኞች ይገኙበት እንደነበረ ታውቋል።

ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት ጄት አዲስና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የደረሰው ባለፈው ኅዳር ሲሆን የዛሬው አደጋ ከመድረሱ በፊት አብራሪው የቴክኒክ ችግር እንደገጠመው አሳውቆ ወደ ቦሌ ለመመለስ ፍቃድ እንዲሰጠው ጠይቆ እንደነበር በአደጋው ሥፍራ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለጋዜጠኞች መናገራቸው ተዘግቧል።

ጆሞ ኬንያታ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ /ናይሮቢ፤ ዕሁድ፤ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም./
ጆሞ ኬንያታ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ /ናይሮቢ፤ ዕሁድ፤ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም./

አይሮፕላኑን ያበርሩ የነበሩት ካፕቴን የረዥም ጊዜ ልምድ የነበራቸው መሆኑን የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ አቶ አሥራት በጋሻው ለቪኦኤ ተናግረው መንስዔውና የአደጋው ዓይነት እየተጣራ መሆኑን ገልፀዋል።

አይሮፕላኑ ባለፈው ዕሁድ ከጆሃንስበርግ መንገደኞችን አሳፍሮ አዲስ አበባ አርፏል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት በመንግሥቱና በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ለተጎዱ ቤተሰቦች ጥልቅ ኀዘኑን በትዊተር ባሠራጨው መልዕክት አሳውቋል።

ቦይንግ ኩባንያ ዛሬ ባወጣው ባለአንድ አረፍተ-ነገር መግለጫ ስለአደጋው ሪፖርት የደረሰው መሆኑንና ሁኔታውን በቅርብ እንደሚከታተል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለጋዜጠኞች የሰጡትን መግለጫ ከሥር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ። /እንግሊዝኛ/

የሪፖርተሮቻችንን ተጨማሪ ዘገባዎችና ቃለ-ምልልሶችን በፌስ ቡክ ገፃችን @voaamharic ላይ ያገኛሉ። ሁኔታውን እየተከታተልን ማውጣት እንቀጥላለን።

የኢቲ-302 ተሣፋሪዎች ቁጥርና ሃገሮቻቸው

የኢቲ-302 ተሣፋሪዎች ቁጥርና ሃገሮቻቸው
የኢቲ-302 ተሣፋሪዎች ቁጥርና ሃገሮቻቸው

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG