ዋሽንግተን ዲሲ —
ይህ በአለም የኢትዮጵያን ስም ያስጠራ አትሌት ታሞ አልጋ ከያዘ ሁለት አመታት ሊያስቆጥር ነው። ሁለቱም ሳምባዎቹ ከፍተኛ ህክምናን ይሻሉ። ህክምናውን ካናዳ ቶሮንቶ ሆስፒታል ውስጥ በመከታተል ላይ ይገኛል። ከትላንት በስትያ ህይወቱ እንዳለፈ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተገልፆ ነበር። ሻምባል ምሩፅ ይፍጠር ህይወቱ አላለፈም፤ በተሻለ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ባለቤቱ ወ/ሮ ርሻን ስልክ ላይ በመደወል አረጋግጠናል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ።