በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‘በኤች አይ ቪ መቆጣጠሪያ መድሃኒት ላይ የሚደረገውን ጥናት በሰፊው ልንቀጥል ይገባናል’ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ ባን-ኪሙን


File-photo AIDS conference in South Africa Durban
File-photo AIDS conference in South Africa Durban

በአለማችን ስድስት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በየቀኑ፤ ወደ ሁለት ሚልየን የሚጠጉ ሰዎች በየዓመቱ በቫይረሱ እየተያዙ እንደሆነና ይህንን ለመቆጣጠር አሁንም የበለጠ መሰራት እንዳለበት ጉባዔው ጠቅሷል።

የአለም አቀፉ የእርዳታ ድርጅት ግሎባል ፈንድ ለ9.2 ሚልየን በ2015 መገባደጃ፤ በተጨማሪም መቶ ሺህ ለሚሆኑ ቫይረሱ በደማቸው ለተገኘባቸው ሰዎች በየወሩ እስከ 2015 አጋማሽ ድረስ መድሃኒትን በማሰራጨት ሲሰራ ቆይቷል።

በደቡብ አፍሪካ ደርባን እየተካሄደ ያለው የአለም አቀፉ የኤች አይ ቪ ኤድስ ጉባዔ ላይ በደማቸው ኤች አይ ቪ ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች የህግ ከለላ እንደሚያፈልጋቸው ተገልጾአል። ጉባዔው ዘንድሮም ትኩረት ሰጥቶ የተነጋገረው በሴተኛ አዳሪነት የሚተዳደሩ ሴቶችና አዳጊ ወጣቶችን ከቫይረሱ በመከላከል ዙሪያ ላይ ነው።እ.አ.አ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በተለይም በአፍሪካ በርካታ ወጣቶች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ማጣታቸው አይረሳም። የቪኦኤ ባልደረቦቻችን ከደቡብ አፍሪካ ደርባን ያደረሱንን ዘገባ አክለን ከኢትዮጵያ የሚመለከታቸውን የጤና ባለሙያዎች በስልክ መስታወት አራጋው አነጋግራለች። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG