በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዋጁ የተጣለው ለስድስት ወራት ነው


 አቶ ሲራጅ ፈጌሳ - የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር
አቶ ሲራጅ ፈጌሳ - የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ለስድስት ወራት ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሣ ገለፁ። አዋጁ ለመጭዎቹ ስድስት ወራት ተግባራዊ ሆኖ የሚቆየው በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ እንደሚሆንና በሁሉም አካባቢዎች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ አመልክተዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ለስድስት ወራት ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሣ ገለፁ።

አዋጁ ለመጭዎቹ ስድስት ወራት ተግባራዊ ሆኖ የሚቆየው በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ እንደሚሆንና በሁሉም አካባቢዎች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ አመልክተዋል።

መግለጫው “ከብሔራው የደህንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ” የሚል ሲሆን፤ መግለጫውን የሰጡት ደግሞ የመከላከያ ሚኒስትሩና የብሔራዊው የደኅንነት ምክር ቤት ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ናቸው።

ዐዋጁን የሚያስፈፅም አዲስ ኮማንድ ፖስት እንደሚቋቋምም ሚኒስትሩ የተናገሩ ሲሆን ሰብሳቢው የሚሆኑትም እራሳቸው የመከላከያ ሚኒስትሩ እንደሚሆኑ ታውቋል።

በዐዋጁ የተጣሉ ክልከላዎች “ማንኛውንም ሁከትና ብጥብጥ ማድረግ፣ በሕዝቦች መካከል መጠራጠርን እና መቃቃርን የሚፈጥር ይፋዊም ሆነ ድብቅ ቅስቀሳ ማድረግ፣ ፅሑፍ ማዘጋጀት እና አትሞ ማሠራጨት፣ ትእይንት ማሣየት፣ በምልክት መግለፅ ወይም መልዕክትን በማንኛውም ሌላ መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ”መሆናቸውን የመከላከያ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

የሚቋቋመው ኮማንድ ፖስት አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን “ማንኛውንም የመገናኛ ዘዴ ሊዘጋ ወይም ደግሞ እንዲቋረጥ ሊያደርግ ይችላል፣ የአደባባይ ሰልፍ፣ መደራጀት እና በቡድን ሆኖ መንቀሳቀስን ይከለክላል” ብለዋል አቶ ሲራጅ ፈጌሳ።

በተጨማሪም፤ “ወንጀል ተፈፅሟል ብሎ ሲያምን ኮማንድ ፖስቱ በማንኛውም ጊዜና ሰዓት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ ፍተሻ ሊያደርግ፣ ሊያስቆምና ሊበረብር ይችላል” ተብሏል።

አቶ ሲራጅ ከመግለጫው በኋላ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ በሰጡበት ወቅት “የመፈንቅለ-መንግሥት ሁኔታ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል አይኖርም” ብለዋል።

የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ሐሳብ ስለሚያቀርቡ አካላትም ተጠይቀው “አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በሕዝብ የተመረጠ በመሆኑ የሽግግር መንግሥት አያስፈልግም” ብለዋል።

መርማሪ ቦርድ እንደሚቋቋምና የሰዓት ዕላፊ ገደብ ተፈፃሚ የሚሆንበት ሁኔታ እንደሚወሰን ሚኒስትሩ ገልፀው የዐዋጁን ጊዜ ማራዘም ካስፈለገም ፓርላማው ሁኔታውን ገምግሞ ለአራት ወራት ሊያራዝመው እንደሚችል አስታውቀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዙትን የድምፅና የቪድዮ ዘገባዎች ያዳምጡ፣ ይመልከቱ።

አዋጁ የተጣለው ለስድስት ወራት ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:40 0:00
አዋጁ የተጣለው ለስድስት ወራት ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:56 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG