በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ "ኢንተርኔትን" በውድ ዋጋ የምትሸጥ ሀገር ተብላለች


አቅም ተመጣጣኝ የሆኑ የኢንተርኔት አገለግሎት አቅርቦት ጥምረት (Alliance for affordable internet)ጥናት ደረጃ
አቅም ተመጣጣኝ የሆኑ የኢንተርኔት አገለግሎት አቅርቦት ጥምረት (Alliance for affordable internet)ጥናት ደረጃ

አቅም ተመጣጣኝ የሆነ የኢንተርኔት አገለግሎት አቅርቦት ጥምረት (A4AI)የተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራትን የኢንተርኔት አቅርቦት ባወዳደረበት ጥናቱ ከ58 ሀገራት ኢትዮጵያን 55ኛ ደርጃ ላይ አስቀምጧታል። ለቪኦኤ ቃለምልልስ የሰጡ የተቋሙ አጥኒ አንድ ሰው 1GB የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ከገቢው ከሁለት በመቶ በላይ ማውጣት እንደሌለበት ገልጸው "በኢትዮጵያ ግን ከወር ገቢው ከ20 በመቶ በላይ" ወጪ ማድረግ ይጠይቃል" ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተተቃሚዎች አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያወጡት ወጪ በጣም ውድ መሆኑን ለአቅም ተመጣጣኝ የሆኑ የኢንተርኔት አገለግሎት አቅርቦት ጥምረት (Alliance for affordable internet) የተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት ጥናት አመለከተ።

ኢትዮጵያ "ኢንተርኔትን" በውድ ዋጋ የምትሸጥ ሀገር ተብላለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:16 0:00

ተቋሙ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራትን ባወዳደረው ጥናቱ ከ58 ሀገራት ኢትዮጵያን 55ኛ ደርጃ ላይ አስቀምጧታል።

የድርጅቱ ከፍተኛ አጥኒዎች ቡድን ኃላፊ ዶናራሽ ታኩር ለአሜሪካ ድምጽ ሲናገሩ አንድ ሰው 1GB የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ከገቢው ከሁለት በመቶ በላይ ማውጣት እንደሌለበት ገልጸው “በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ለመሆን ከወራህዊ ገቢ ላይ 20 በመቶ ወጪ ማድረግ ያስፈልጋል” ብለዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኔኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አሕመድ በበኩላቸው፤ “ በሁለት መንገድ መረጃው ትክክለኛ አየደለም” ሲሉ መከራከሪያ ያርቀባሉ።

በኦሬገን ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን የዶክትሬት ጥናታቸውን በማገባደድ ላይ የሚገኙት አቶ እንዳልካቸው ጫላ በበኩላቸው “ እንዲህ ያሉ ጥናቶች የተጨበጠ የተጠቃሚ መረጃን መሰረት አድርገው የሚሠሩ በመሆናቸው ለመካድም ሆነ ለማስተባበል የሚመቹ አይደሉም” ይላሉ።

ጽዮን ግርማ ሁሉንም ወገን አነጋግራ ዘገባ አጠናቅራለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG