አዲስ አበባ —
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣውና ለኢትዮጵያ ፓርላማ የቀረበው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ፣ ዛሬ “ያልተለመደ” ከሚባል ሰፊ ተቃውሞ ጋር ፀድቋል፡፡
የድምፅ አሰጣጡ በአራቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለውን ልዩነት አደባባይ ያወጣ እንደሆነም የገለፁም አሉ፡፡
የኦሮምያን ክልል የሚወክሉ ዘጠና አምስት የፓርላማ አባላት የዐዋጁን መፅደቅ አልደገፉም፡፡ ሰማኒያ ስምንቱ ተቃውመዋል፣ ሰባቱ ደግሞ ድምፀ ተዓቅቦ አድርገዋል፡፡
ሙሉውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ