በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል መግለጫ

Members of parliament
Members of parliament

ዛሬ የኢትዮጵያ ፓርላማ ያፀደቀውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ ዓለምቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወዲያውኑ ባወጣው መግለጫ ውሣኔውን “አሳዛኝ እና ኃላፊነት የጎደለው” ብሎታል።

ዛሬ የኢትዮጵያ ፓርላማ ያፀደቀውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ ዓለምቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወዲያውኑ ባወጣው መግለጫ ውሣኔውን “አሳዛኝ እና ኃላፊነት የጎደለው” ብሎታል።

መግለጫው አክሎም የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት “የህዝቦችን ቅሬታዎች ከማዳመጥ ይልቅ መሠረታዊ መብቶቻቸውን መገደብን መርጠዋል” ብሏል።

የፖለቲካ ውጥረትና ተቃውሞ ባለበት በአሁኑ ወሳኝ ወቅት ለኢትዮጵያ የሚያስፈልገው ሰብዓዊ መብቶችን ማክበር ነው ሲልም አምነስቲ አያይዞ አስገንዝቧል፡፡

“ባለፈው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ህገወጥ ግድያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈፀማቸውን መዝግበናል፤ ዜጎችን ከቀያቸው በግድ ማፈናቀል፣ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሰር እና የሥቃይ አያያዝ መፈጸም ከጥሰቶቹ መካከል ይጠቀሳሉ ብሏል አምነስቲ ኢንተርናሽናል በመግለጫው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG