በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመገናኛ ብዙሃን አሰራር ላይ የተደረገ ውይይት - ክፍል አንድ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ አመራሩ ከዘለቁ ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰቱ አዎንታዊ እርምጃዎች አንዱ በመገናኛ ብዙኃን ላይ ማነቆ ሆኖ የቆየው ህግ መወገድ ነው። ህጉ ላይ መሻሻል እየተደረገ ሲሆን ለጊዜው የመናገር ነፃነት በአገሪቱ ሰፍኗል።

በድፍን ዓለም ጋዜጠኞችን በማሰር በድፍን ዓለም በቀዳሚነት ትጠራ የነበረች ሃገር ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ከእሥር በመልቀቅ የመናገር ነፃነት ታጋዮችን አስደምማ የዓለም የነፃ ፕሬስ ቀን በምድርዋ እንዲከበሩ ሆኗል።

ከዚህ በተጨማሪ ጋዜጠኞች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸው የኢንተርኔት፣ የራድዮና የቴሌቪዥን የብዙኃን መገናኛ ሥርጭት ይዘዋል።

እንዲያ ሆኖ ታዲያ መገናኛ ብዙኃኑ ኃላፊነታቸውን በትክክል እየተወጡ ነው? አገሪቱ በፖለቲካ ሽግግር ላይ መሆኗ ሲጤን በዜና ሥርጭት መስክ ከተሠማሩት፣ እንዲሁም ከመንግሥት ምን ይጠበቃል?

ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ያለመ በትናንት ምሽት ጀምረናል። ተወያዮቹ የፎርቹን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ታምራት ገብረጊዮርጊስ፣ የመገናኛ ብዙኃን ሕጎች ማሻሻያና ጥናት ቡድን ሰብሳቢ አቶ ሰሎሞን ጎሹ እና በመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት የሚድያ ብዝኃነት ዳይሬክተር አቶ ታምራት ደጀኔ ናቸው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የመገናኛ ብዙሃን አሰራር ላይ የተደረገ ውይይት - ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:08 0:00
የመገናኛ ብዙሃን አሰራር ላይ የተደረገ ውይይት - ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:29:31 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG