ዋሺንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያ ውስጥ ተቃውሞው ሃገሪቱን ያጥለቀለቀው ሕዝቡ የመንግሥትን ባዶ ቃሎች ሳይሆን እውነተኛ ለውጥ ማየት ስለሚፈልግ ነው ሲሉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና አሳሰቡ፡፡
መንግሥት የፖለቲካ ለውጦችን አመጣለሁ ሲል ሰሞኑን ማሳወቁ የዘገየ መግለጫ ነው ብለውታል፡፡
“ዴሞክራሲያዊ መንግሥት እስኪመሠረት፣ ሁሉንም ዜጎች የሚያሣትፍ የፖለቲካ ሥርዓት በሃገሪቱ እስኪፈጠር፤ ምንም ቢያስከፍለን ትግላችን ይቀጥላል” ብለዋል ዶ/ር መረራ ጉዲና በዚሁ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፡፡
ከናይሮቢ የደረሰን የሪፖርተራችን የጂል ክሬግ ዘገባ አለ፤ ሰሎሞን አባተ ያቀርበዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡