በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ነዋሪዎች ስለ ዛሬው የጎንደር ውሎ ይናገራሉ


ጎንደር ከተማ
ጎንደር ከተማ

በጎንደር ከተማ በነዋሪዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት በመንግስት ታጣቂዎች ሕይወታቸው ያለፈ አቶ ሲሳይ ታከለ የተባሉ አንድ አዛውንት የቀብር ሥነ ስርዓት በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ መፈጸሙን ነዋሪዎች ይናገራሉ። መንግሥት በግጭቱ አምስት ሰዎች በተባራሪ ጥይት ሕይወታቸው ማለፉን አስታውቋል።

ሐምሌ አራት ለሐምሌ አምስት አጥቢያ የፌደራል ልብስ ለብሰው ጭንብል ያጠለቁና ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማነንት ጥያቄ ኮሚቴ አራት አባላትን አፍነው በመውሰዳቸና፤ አንዱን የኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በግዳጅ ለመውሰድ በተደረገ ግብግብ በጎንደር ከተማ ግጭት መጫሩ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ የኮሚቴው ፀሐፊ አቶ አደራጀው ናኘው ተናግረዋል።

የጎንደር ከተማ
የጎንደር ከተማ

በዚህ መነሻ በተፈጠረው ግጭት ትናንትና እና ከትናንት በስቲያ ከመንግሥትም ከሕዝቡም የሰው ሕይወት መጥፋቱን ሁለቱም የሚያምኑ ሲሆን በሕዝቡ በኩል የተረጋገጠ የሟቾች ቁጥር የለም። በመንግሥት በኩል አምስት ሰዎች በተባራሪ ጥይት ሕይወታቸው ማለፉን አስታውቋል። በሕዝቡ በኩል ምን ያህል ሰው ሕይወት እንደጠፋ የተረጋገጠ ቁጥር የለም የኮሚቴው ፀሐፊ አቶ አደራጀው ናኘው በትናንትናው ዕለት ለጣቢያችን እንደተናገሩት ትናንት ከሕዝቡም ከመንግስትም የሞቱ ሦስት ሰዎች ቀብር ተፈጽሟል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ በግጭቱ ሕይወታቸውን ያጡ አቶ ሲሳይ ታከለ የተባሉ አዛውንት የቀብር ሥነ ስርዓት ተፈጽሟል።

የአሜሪካ ድምጽ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የወልቃይት ተወላጆችና የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችን አነጋግሮ ላጠናከረው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ነዋሪዎች ስለ ዛሬው የጎንደር ውሎ ይናገራሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:38 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG