በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ክፍል 1፡ "ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ" ዝግጅት የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ዕድር


የአክሱም ቄስ ታቦት ተሸክመው [ፋይል ፎቶ - አሶሽዬትድ ፕረስ/AP]
የአክሱም ቄስ ታቦት ተሸክመው [ፋይል ፎቶ - አሶሽዬትድ ፕረስ/AP]

ደብረ-ሰላም ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ዕድር ይባላል። ኢትዮጵያውያን ሲሞቱ አስከሬን መሸኛ፣ ወገን ሲቸገር መርጃ እየተባለ በየጊዜው "ዣንጥላ ማዞሩ ሰለቸን" ያሉ አባላት ነበሩ ሃሳቡን አመንጭተው ያቋቋሙት። በወቅቱ ቤተ-ክርስቲያኒቱም እገዛና ፍቃዷን ሰጥታለች። የዕድሩን አመራር አባሎችና በስፍራው የተገኙ ኢትዮጵያውያንን ያወያየ ዝግጅት።

ደብረ-ሰላም ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ዕድር ከቤተ-ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ወጥቶ የራሱን ጽ/ቤትና መሰብሰቢያ አዳራሽ ገዝቶ ባለፈው እሑድ አስመርቛል። ከ500 የማያንሱ ኢትዮጵያውያን በምረቃው ላይ ተገኝተው ቤት ለእንቦሳ ብለዋል፣ ደስታቸውንም ገልጸዋል።

በዲሲዋ ደብረ-ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ተቋቋመ፣ የዛሬ 15 ዓመት። "ቀላል የማይባል እጅግ ብዙ ውጣ-ውረድ፣ ፈታኝ ፈተናና እልህ አስጨራሽ ጉዞ አድርጎ ነው፣ ለራሱ ጽ/ቤት ብቻ አይደለም፣ ከራሱም አልፎ ብዙ ኢትዮጵያውያን በደስታም ሆነ በኃዘን የሚሰባሰቡበት፣ አቅመ-ደካሞች የሚያርፉበት፣ ሙኣለ-ህፃናት ሊቋቋም የሚችልበት ህንፃ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጎ የገዛው" ይላሉ አመራሮቹ።

በአመራሩ ብዙ የቆዩትና ለአገልግሎታቸውም በብዙ አባሎች የተመሰገኑት ሊቀ-መንበሩ አቶ ታደለ አወቀ፣ "ይህ፣ ለሁሉም የዕድሩ አባሎች ከእግዚአብሔር የተቸረ ስጦታ ነው" ብለዋል።

"ጥቅሙ ለእኛ ብቻም አይደለም፣ መዋል በማይገባቸው ቦታ የዋሉ ልጆቻችንንም ይሰበስብልናል"ይላሉ ምክትል ሊቀ-ንበሩ አቶ አምኃ ሥዩም በበኩላቸው።

እናም "እርዱን" ብለዋል አቶ አምኃ። "የምን እርዳታ?" ቢባል፣ ህንፃው ያላለቀ ሥራ ስላለው ያን ማስጨረሻ መሆኑ ነው። አዎ፣ ተዘዋውረን እንዳየንው ይህ ህንፃ ነገውኑ ሥራ ይጀምራል፣ ነገውኑ ሕዝብ ይሰበሰብበታል፣ ነገውኑ ኃዘነተኛ ይቀመጥበታል ማለት አይቻልም፣ የሚቀር ሥራ አለውና።

ቦታውን በተመለከተ ሊቀ-መንበሩ አቶ ታደለ እንደገለጹት ሰፊ የመሬት ይዞታ ስላለው፣ ግቢው ውስጥ ቢያንስ ሃምሳ መኪኖች ሊቆሙ ይችላሉ። ከግቢው ወጣ ብሎ ባለው የራሱ ሰፊ ሜዳ ላይ ደግሞ ከሰባ በላይ መኪኖች ማቆም ይቻላል። ይሄ ደግሞ፣ በቅርብ የእግር ጉዞ ካለበትና ቅዳሜና እሑድም በነፃ ማቆም ከሚቻልበት በተጨማሪ መሆኑ ነው። ይህ ብቻ አይደለም። "ማንኛውም የዕድሩ አባል" ይላሉ አቶ ታደለ፣ "በሥራ ጓደኞቼ ጠንካራ ሥራና ብርቱ ትጋት በጣም መደሰቴን ለመግለጽ እፈልጋለሁ" ያሉት የዕድሩ ጸሓፊ ወ/ዕሌኒ ለገሠ፣ አጭሩን ንግግራቸውን የደስታ ሲቃ አቋርጧቸዋል።

አቶ አክሊሉ መኰንን ኦዲተር ናቸው። ዘለግ ያለውን ምስጋና ለሊቀ-መንበሩ ይሰጣሉ። ሥራው ቢያጣልንም፣ ቢያጨቃጭቀንም፣ ጠቡ ከሥው ጋር በተያያዘ በመሆኑ የዕለቱ ሥራ ሲያበቃ ጭቅጭቁና ቁጣው አብሮ ያበቃል ይላሉ።

በምረቃው ሥነ-ሥርዓት የተገኙ አባላትንና የተጠሩ እንግዶችንም ከቤተ-ክርስቲያኒቱ የበላይ ጠባቂ ሊቀ-ሊቃውንት ወርቅነህ ኃይሌ እስከ አባል ምዕመን ድረስ ነበሩ። ሊቀ-መንበሩ አቶ ታደለ አወቀም በሥነ-ሥርዓቱ ተገኝተው ነበር።

በራሳቸው በአባላቱ እንደተገለጸው፣ በተለይ በሜሪላንዷ ሲልቨር ስፕሪንግ (Silver Spring) መሓል ከተማ ይህን ህንፃ ማግኘት፣ እውነት ነው፣ ቀላል አይደለም፤ ብርቱ ጥረት የጠየቀ ነው። ለነገሩ እንደ ዕድሩ የ15 ዓመት ዕድሜ አይደለም፣ ከተቋቋሙ ከአርባ ዓመት በላይ የሆናቸው የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማዕከል ጽ/ቤቶች አሉ፣ ስንቶቹ ናቸው ይህን ያደረጉ? በዕድር ደረጃ ደግሞ፣ ከመላው ዩናይትድ ስቴትስ፣ የራሱን መሰብሰቢያ አዳራሽ የገዛ፣ ባለን መረጃ መሰረት፣ ይሄ የመጀመራው ነው።

ሆኖም ታዲያ፤ የደብረ-ስላሙ መረዳጃ ዕድር ጽ/ቤት ብዙ ይቀረዋል። ምቹ የመኪና ማቆሚያ፣ በደስታም ሆነ በኃዘን ጊዜ፣ ኢትዮጵያውያን በብዛት ሲሰባሰቡ ማስተናገድ የሚችል ስፍራ ያስፈልጋል።

ህንፃው በ$1,350,000 እንደተገዛ አቶ ታደለ ቀደም ሲል ገልጸዋል። ቤቱ የግሉ የዕድሩ በመሆኑ የሚያከራየው ክፍልም አለው። ያም ሆኖ ግን ወጪ አለው፤ ማለትም ሞርጌጁ ወይም ወርሃዊ ክፍያው። አቶ ታደለ ሲመልሱ "ይህ ህንፃ የኢትዮጵያዊ ሁሉ ንብረት ነው። ማንኛውም በተለይም አባሉ፣ ከወርሃዊ መዋጮው በተጨማሪ፣ ለህንፃው ማጠናቀቂያ የሚሆነውን በመርዳት፣ ኢንቨስትመንቱን-ንብረቱን የግሉ ማድረግ ይኖርበታል" ብለው፣ ያለበትንም ዕዳ ዘርዝረዋል።

ቀጣዩን 2ኛ ክፍል ለዚህ ጥያቄ በሚያገኘው መልስ ባልደረባችን አዲሱ አበበ ይዞ ይቀርባል። ለአሁኑ 1ኛውን ክፍል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

"ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ" ዝግጅት የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ዕድር ክፍል 1
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:24 0:00


XS
SM
MD
LG