በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ሕጻናት ቁጥር ቀንሷል፤ የአዋቂዎች ቁጥር ግን ለውጥ አላሳየም


በአፍሪካ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ሕጻናት ቁጥር ቀንሷል፤ የአዋቂዎች ቁጥር ግን ለውጥ አላሳየም
በአፍሪካ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ሕጻናት ቁጥር ቀንሷል፤ የአዋቂዎች ቁጥር ግን ለውጥ አላሳየም

ህፃናትን ከቫይረሱ በመከላከል ዙሪያ በሰፊው በመሰራቱ እ.አ.አ በ2001 ዓ.ም ከተመዘገበው የሕፃናት የመያዝ ቁጥር 70 በመቶ ቀንሶ ታይቷል። በኤች አይ ቪ የተያዙ አዳዳዲስ አዋቂዎች ላይ በተደረገው ጥናት ግን በ2010 ዓ.ም ከተመዘገበው ቁጥር ጋር ሲተያይ ምንም አይነት ለውጥ አላሳየም። ለአምስት አመታት ቁጥሩ 1.9 ሚልየን ላይ ቆይቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ቢሮ በኤች አይ ቪ መስፋፋት ዙሪያ የተሻለ ለመስራት ጥሪ አቅርቧል። እ.አ.አ. 1997 ዓ.ም በአለም አቀፍ ደረጃ በተደረገው ጥናት፤ በጥቅሉ አዋቂዎችና ልጆች በኤች አይ ቪ የመያዝ ዕድላቸው ከተመዘገበው አጠቃላይ ሶስት ሚልየን ከሚሆነው ቁጥር 40 በመቶ ያህሉ ቢቀንስም ቁጥሩ አጥጋቢ አልሆነም።

ዘገባው እንደሚያመለክተው ከሰሃራ በስተደቡብ የአፍሪካ ሃገሮች የሚገኙ ወጣት ሴቶች ለኤች አይ ቪ በጣም የተጋለጡ ናቸው። በቅርቡ 75 በመቶ የሚሆኑት የኤች አይ ቪ የተገኘባቸው ከ10-19 እድሜ ላይ የሚገኙ ወጣት ሴቶች ናቸው ።

በኤች አይ ቪ የመያዝ ቁጥሩ መጨመር አሳሳቢ የሆነው የህብረተሰብ ክፍል ፤ በተመሳሳይ የፆታ የግብረስጋ ግንኙነት በተለይም በወንዶች መካከል፣ በሴተኛ አዳሪነት የሚተዳደሩና የነሱ ደምበኞች እንዲሁም በመርፌ የአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚዎች እና በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ናቸው።

እ.አ.አ በ1985 ዓ.ም የተመሰረተው አለም አቀፉ የኤድስ ኮንፈረንስ 180 የሚሆኑ ሃገሮች ይሳተፉበታል። ይህ ስብሰባ በደርባን ደቡብ አፍሪካ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ይካሄዳል። ይህንን አለም አቀፍ ስብሰባ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ደቡብ አፍሪካ በደርባን የምታስተናግደው።

ሊሳ ስህን የዘገበችውን መስታወት አራጋው ታቀርበዋለች። ሙሉ ዘገባውን ለመስማት ከበታች ያለውን ድምፅ በመጫን ያድምጡ።

በአፍሪካ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ሕጻናት ቁጥር ቀንሷል፤ በአዋቂዎች ላይ ግን ቁጥሩ ለውጥ አላሳየም
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:32 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG