በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ያስተላልፋል ተብሎ የተያዘው የመድሃኔ ተስፋማሪያም አጠያያቂ ማንነት


በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ያስተላልፋል ተብሎ የተያዘው የመድሃኔ ተስፋማሪያም ኪዳነ
በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ያስተላልፋል ተብሎ የተያዘው የመድሃኔ ተስፋማሪያም ኪዳነ

"በህገወጥ መንገድ ስደተኞችን ከሃገር ወደ ሃገር በማስተላለፍ ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘው ግለሰብ በወንጀለኝነት የሚፈለገው ትክክለኛው ሰው አይደለም" የሚሉ ድምፆች እየተሰሙ ነው። ተጠርጣሪውን መከታተልና በቁጥጥር ስር በማዋሉ ስራ የተሳተፉት የብሪታንያንና የጣልያን የደህንነት ባለስልጣናት በበኩላቸው በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ምርመራ መያዛቸው ተዘግቧል።

በመንገድ ላይ ያለቁትንና ባህር የበላቸውን ጨምሮ ከአቅማቸው በላይ በታጨቁ ጀልባዎች ላይ በላይ በላዩ እየጫነ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ ጣልያን በመላክና ሌሎች ወንጀሎችን በመፈፀም የሚፈለገው ግለሰብ መያዙን ይፋ ያደረጉ የፎቶግራፍና የቪዲዮ ምስሎች እንደወጡ ነው አወዛጋቢው ዜና የተከተለው።

"ይፈለጋል” የተባለው እርሱ አይደለም፤ ሲሉ ከካርቱም ላይ የተያዘው የ27 አመቱ ኤርትራዊ የመድሃኔ ተስፋማሪያም ኪዳነ የቤተሰብ አባላትና የቅርብ ጓደኞች ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃል መሟገት የያዙት።

አማኑአል ዘይድ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በአስመራ ከተማ ገዛማንዳ ጣልያን የሚባል ሰፈር ነው። በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ያስተላልፋል በማለት ጣልያኖች ከያዙት ከመድሃኔ ተስፋማሪያም ጋር በአንድ ሰፈር ነው እንዳደጉና ሱዳን በስደት ላይም በአንድ ቤት ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ይናገራል።

መድሃኔ ተስፋማሪያም ኪዳነ
መድሃኔ ተስፋማሪያም ኪዳነ

ሜሮን እስጢፋኖስ በአውሮፓ የስደተኞችን ጉዳይ በመከታተል ይታወቃሉ፡ ቀደም ሲል የሚፈለገው ሰው ፎቶ ግራፍ ወጥቶ እንደነበርና ኋላ ላይ የተያዘው ሰው ፎቶግራፍና በዜና ዘገባዎች እንደወጣ ነው አስደንጋጩን ስህተት የተረዳሁት፤ ይላሉ።

ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያድምጡ።

በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ያስተላልፋል ተብሎ የተያዘው የመድሃኔ ተስፋማሪያም አጠያያቂ ማንነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG