በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍቅርተ አዲስ ‘የፍቅር ዲዛይን” መስራችና ባለቤት


ፍቅርተ አዲስ ‘የፍቅር ዲዛይን” መስራችና ባለቤት
ፍቅርተ አዲስ ‘የፍቅር ዲዛይን” መስራችና ባለቤት

የሶስት ልጆች እናት ናት። ፍቅርተ አዲስ ትባላለች፤ የፍቅር ዲዛይን ባለቤትና መስራች ናት። ልብስን ዲዛይን ማድረግና መስፋት ከልጅነቷ የምትተገብረው የትርፍ ጊዜ ስራዋ ነበር።

ፍቅርተ አዲስ በአጫጭር ጊዜ የስፌትና ቅድ ትምህርቶች በመታገዝ የኢትዮጵያን የባህል ልብሶች በአዳዲስ ፈጠራ በማቅረብ በበርካታ የባህል ልብስ አድናቂ ዘንድ ተመራጭ ሆናለች።

የመጀመሪያ ዲግሪዋንና የከፍተኛ ትምህርቷን በስነልቦና ጥናት (በሳይኮሎጂ) አጠናቃለች። በተማረችበት ሙያ ለተወሰኑ አመታት ከሰራች በኃላ ወደምትወደው የልብስ ስፌትና ቅድ እንዲሁም የልብስ ዲዛይን ፈጠራ ስራ ላይ ሙሉ ትኩረቷን አድርጋ በመስራት ላይ ትገኛለች። የምትሰራቸው ልብሶች የኢትዮጵያን የባህል ልብስ መሰረት ያደረገ ሆኖ በአዲስና በዘመናዊ መልክ የሚሰራ ነው።

some of Fikirte Addis works
some of Fikirte Addis works

ፍቅርተ አዲስ ለልብስ ቅድና ስፌት የምትጠቀምባቸውን የኢትዮጵያን ባህላዊ ጨርቆች ከሚያመርቱ ሸማኔዎች ጋር ያላት ግንኙነት በስራ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ከራስዋ ስኬት አልፋ በሽመና ሙያ ለሚተዳደሩት ቤተሰቦችና ልጆቻቸው ስኬት ትተጋለች። በተለይም በሽመና ስራ ላይ የሚታየውን የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን ለመከላከል በስነ-አእምሮ ወይም በስነ-ልቦና ምርምር (ሳይኮሎጂ) ሙያዋ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ትገኛለች። ከመስታወት አራጋው ጋር ያደረገችውን አጭር ቆይታ ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያድምጡ።

ፍቅርተ አዲስ ‘የፍቅር ዲዛይን” መስራችና ባለቤት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:05 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG