No media source currently available
የሶስት ልጆች እናት ናት። ፍቅርተ አዲስ ትባላለች፤ የፍቅር ዲዛይን ባለቤትና መስራች ናት። ልብስን ዲዛይን ማድረግና መስፋት ከልጅነቷ የምትተገብረው የትርፍ ጊዜ ስራዋ ነበር። በአጫጭር ጊዜ የስፌትና ቅድ ትምህርቶች በመታገዝ የኢትዮጵያን የባህል ልብሶች በአዳዲስ ፈጠራ በማቅረብ በበርካታ የባህል ልብስ አድናቂ ዘንድ ተመራጭ ሆናለች።