በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ የፋሽን ጥበብ ባለሙያዎች ብርቱ እገዛ ያስፈልጋቸዋል


የቀድሞ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሞዴል አና ጌታነህ (Anna Getaneh)
የቀድሞ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሞዴል አና ጌታነህ (Anna Getaneh)

"የኢትዮጵያ የፋሽን ጥበብ ባለሙያዎች ካገር ውስጥ ብርቱ እገዛ ያስፈልጋቸዋል" የቀድሞ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሞዴል አና ጌታነህ።

ኦሪጂን ኣፍሪካ 2015 የተሰኘው ዓለም ኣቀፍ ኣውደ ርዕይ ባለፈው ሳምንት እ ኤ አ ጥቅምት 21 እስከ ጥቅምት 23 አዲስ አበባ ውስት ተካሂዱዋል። የጥጥ ፡ የጨርቃ ጨርቅ እና ከቆዳና ከልዩ ልዩ ጥሬ ዕቃዎች የሚሰሩ የቤት ማስዋቢያ ቁሳቁሶች ማስተዋወቂያ ዋና መድረክ የሆነው ይህ ዓመታዊ አውደ ርዕይ ሲዘጋጅ አምስተኛ ጊዜው ነው። ከዚህም በላይ በምርት መገኛነትና በመዋዕለ ነዋይ መዳረሻነት የሚያገለግል፡ ገዢዎች፡ ነጋዴዎች፡ መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾችና የኣውደ ርዕይ ባለሙያዎችን የሚያሰባስብ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ኣዘጋጆቹ ገልጸዋል።

በሶሥቱ ቀናት አውደ ርዕይ ወቅት የኣፍሪካ የጥጥ ምርት ዕድገት፡ የተራዘመው የዩናይትድ ስቴትስ የኣፍሪካ ንግድ ተጠቃሚነት ድንጋጌ AGOA በቀጣዮቹ ኣስር ዓመታት የሚያስገኘው ዕድልና የሚኖሩት ፈተናዎች ላይ ሴሚናሮች ተካሂደዋል። የአፍሪካን ዘመናዊ ፋሺን፡ የቤት ቁሳቁስና ጌጣጌጥ ዘርፍ ማስፋፋት አፍሪካውያን ዲዛይነሮች በዓለም ኣቀፍ ገበያዎች ያላቸውን ተወዳዳሪነት ማሳደግ ስለሚቻልበት መንገድም ውይይት ተደርጉዋል።

በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው ኦሪጂን አፍሪካ 2015 አውደ ርዕይ ከአንድ መቶ ሰማኒያ ኣምስት የማያንሱ ኩባኒያዎች ፡ ከሃያ ሰባት የሚበልጡ የአውሮፓ የአሜሪካና የእስያ እና የኣፍሪካ ሃገሮች ተካፍለዋል።

የአፍሪካን ፋሺንና ባለሙያዎቹን በአለም ኣቀፍ ገበያዎች ማስተዋወቅን ኣስመልክቶ በተካሄደው ውይይት ላይ ተሳታፊ የነበረችው ዕውቁዋ ዓለም ኣቀፍ ሱፐር ሞዴል አና ጌታነህ ከቪኦኤ ዘጋቢ ጋር ያደረገችውን ቆይታ ያድምጡ።

የቀድሞ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሞዴል አና ጌታነህ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:16 0:00

XS
SM
MD
LG