በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚሰጥበት አዲሱ የጊዜ ሰሌዳ ሁሉንም አስማምቷል


የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ለአንድ ሳምንት ማራዘሙ ሀገር ውስጥ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል። ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፈተናው ከረመዳን ጾም ፍቺ በኋላ እንዲሰጥ በመጠየቁ ነው ብሏል። የአሜሪካ ድምፅ ይህንኑ በተመለከተ በውጭ ሀገር የሚገኙ የኦሮሞ ተቃውሞ አስተባባሪዎች አቶ ጃዋር መሐመድን የድምጻችን ይሰማ የድጋፍ ግብረሃይል አቶ ሳዲቅ አሕመድን አነጋግሯል።

ከዚህ ቀደም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተናው ሾልኮ በመውጣቱና በግንቦት ወር ሊሰጥ የነበረ ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 እንዲሰጥ መወሰኑን ካስታወቀ በኋል ጉዳዩ ለሁለት ሳምንት ሲያወዛግብ መቆየቱ ይታወሳል።

የውዝግቡ ማጠንጠኛም ለፈተናው ሾልኮ መውጣት ኃላፊነቱን ወስደው የነበሩት በውጭ አገር የሚገኙ የኦሮሞ ተቃውሞ አስተባባሪዎች ፈተናው ለሁለት ወር እንዲራዘም ሲጠይቁ፣ በውጭ ሀገር የሚገኙ የድምፃችን ይሰማ የድጋፍ ግብረሃይል አባላት የፈተናው ጊዜ ከረመዳን ጾም እና ፍቺ ጋር የተገናኘ መሆኑን በመግለጽ ሲቃውሙት እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

አሁን የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ለአንድ ሳምንት ማራዘሙ ሀገር ውስጥ ለሚገኙ ብዙሃን መገናኛ አስታውቋል። ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፈተናው ጊዜ ከረመዳን ጾም ጋር የተገናኘ መሆኑን በመግለጽ ለተማሪዎች ከጾሙ በኋላ ፈተናው እንዲሰጥ በመጠየቁ ነው ብሏል።

​ጽዮን ግርማ ይህንኑ በተመለከተ በውጭ ሀገር የሚገኙ የኦሮሞ ተቃውሞ አስተባባሪዎች አቶ ጃዋር መሐመድን እና በውጭ ሀገር ከሚገኙ የድምጻችን ይሰማ የድጋፍ ግብረሃይል አቶ ሳዲቅ አሕመድን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚሰጥበት አዲሱ የጊዜ ሰሌዳ ሁሉንም አስማምቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG