ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን የጠሩትና በሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ ላይ ያተኮረ ጉባኤ የተለያዩ የአፍሪካ፤ የአውሮፓ ህብረት፡ የጀርመን የእንግሊዝና የፈረንሳይ ባለሥልጣናት በተገኙበት በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል።
ከፍተኛ የሚኒስትሮቹን ስብሰባ ተከትሎም የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር በስብሰባው የተንጸባረቀውን አቋም ያጠናከረ መግለጫ አውጥተዋል።
ለሰሜን ኢትዮጵያው ቀውስ ወታደራዊ መፍትሄ የለም ያሉት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል ውይይት እንዲፈታ ጥሪ ያቀረቡበትን ጨምሮ ያካተተ ዘገባ ደርሶናል ቀጥሎ ይቀርባል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡