በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ "ተከሳሾች" የጠበቆቻቸው ምላሽ


ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎ
ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎ

በቂሊንጥ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ተከሰው የሚገኙ እስረኛ ተከሳሾች "እኛ በምስክርነት ልንቆጠር ሲገባ ድርጊቱ ፈፅማችኋል ተብለን መከሰሳችን ይሳዝናል" በማለት ድርጊቱን አለመፈፀማቸውን ገልፀው የእምነት ክሀደት ቃላቸውን ለፍርድ ቤት መስጠታቸውን ጠበቆቻቸው ተናግረዋል።

ነሐሴ 28/2008 ዓ.ም. በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለደረሰው የእሳት ቃጠሎና ለደረሰውን ጉዳት እስረኞቹም ሆነ የማረሚያ ቤቱም አስተዳደና ጠባቂዎች በሕግ ሊጠየቁ ይገባል በሚል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ላወጣው የምርመራ ሪፖርት በዚህ ጉዳይ ተከሰው ፍርድ ቤት በመቅረብ ላይ የሚገኙ የእስረኛ ተከሻሽ ጠበቆች ደንበኞቻቸው ድርጊቱን አለመፈፀማቸውን ገልፀው የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተናገሩ። የማረሚያ ቤቱን ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።

ጽዮን ግርማ ሁለት ጠበቆች አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ "ተከሳሾች" የጠበቆቻቸው ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:50 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG