በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት ጠባቂዎች ወደ እስረኞች ተኩሰዋል" - ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን


የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የቃጠሎ አደጋ በደረሰበት ወቅት
የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የቃጠሎ አደጋ በደረሰበት ወቅት

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሰሳው የእሳት ቃጠሎ ወቅት የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች በእስረኛው ላይ ከውጭ ወደ ውስጥ ተኩሰው እንደነበርና አስለቃሽ ጭስም ወርውረው እንደነበር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ሪፖርት አቀረበ። በዚሁ መሰረት ድርጊቱን የፈፀሙት የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎችና ትዕዛዙን የሰጡት ኃላፊዎች በሕግ ሊጠየቁ ይገባል ብሏል።

ነሐሴ 28/2008 ዓ.ም. በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደረሰው የእሳት ቃጠሎና ለደረሰው ጉዳት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አባላት በሕግ እንዲጠየቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ የፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርት አቅርቧል።

በአተት በሽታ ምክኒያት ምግብ ከውጭ አይገባም በሚለው የማረሚያ ቤቱ ውሳኔ የተበሳጩ የቀጠሮ እስረኞች ባስነሱት አድማ መነሻነት ከውጭ በገቡ እንደ ላይተር ባሉ አቀጣጣይ ነገሮች መነሻነት የተነሳ ቃጠሎ መሆኑን የሚጠቅሰው ሪፖርቱ ቃጠሎው ከደረሰ በኋላ አብዛኞቹ የቀጠሮ እስረኞች ከእሳቱ ራሳቸውን ለማዳን ሲሞክሩ ከውጭ በጥበቃ አባላት የተኩስ እሩምታ እንደተከፈተባቸና አስለቃሽ ጭስም ከውጭ ወደ ውስጥ እንደተኮሰ ተዘርዝሯል።

በተጨማሪም ለማምለጥ የሞከሩ ሁለት እስረኞች በጥይት ተመተው መገደላቸውን ሌሎች ስምንት እስረኞች ቆስለዋል ተብሏል።

ጽዮን ግርማ ሪፖርቱን በተመለከት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሰብዓዊ መብት ምርመራ ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አባዲን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

"በቂሊጦ ቃጠሎ ወቅት ጠባቂዎች ወደ እስረኞች ተኩሰዋል" - ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:55 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG