በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ የሥራ ዘመናቸውን አጠናቅቀው ተሰናበቱ


የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ የሥራ ዘመናቸውን አጠናቅቀው ተሰናበቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:18 0:00

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ የሥራ ዘመናቸውን አጠናቅቀው ተሰናበቱ

በኢትዮጵያ የትጥቅ ግጭቶች “ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዋና ምክንያት ኾነው ቀጥለዋል” ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በሕይወት የመኖር መብትን አሳሳቢ ማድረጉን፣ ዛሬ ዐርብ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ ዶክተር ዳንኤል በቀለ፣ የትጥቅ ግጭቶቹ እያደረሱት ያሉት ዘርፈ ብዙ ሥቃይ “እጅግ እየጨመረ” መኾኑን ገልጸው፣ ብቸኛው መፍትሔ የሰላም ውይይት ነው፤ ብለዋል፡፡

የኮሚሽኑን ሪፖርት ለብዙኀን መገናኛዎች ያቀረቡት ዋና ኮሚሽነሩ ዳንኤል በቀለ፣ የአምስት ዓመታት የሥራ ጊዜያቸውን አጠናቅቀው ተሰናብተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በዶክተር ዳንኤል በቀለ ዋና ኮሚሽነርነት እየተመራ፣ በዓለም አቀፉ የብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት ጥምረት፣ የፓሪስ መርኅዎችን ወይም የተኣማኒነት መለኪያዎችን ለሚያሟሉ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት የሚሰጠውን "A status" ወይም "A ደረጃ" በ2014 ዓ.ም. ታኅሣሥ ወር አግኝቷል።

ዋና ኮሚሽነሩ ዳንኤል በቀለም፣ በቅርቡ የአውሮፓ ኅብረትን የ”ሹማን” ሽልማት፣ እንዲሁም ለሰብአዊ መብቶች መከበር የሕይወት ዘመን አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የሚሰጠውን የጀርመን አፍሪካ ሽልማት ማግኘታቸው ይታወሳል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐዲስ ዋና ኮሚሽነር እስኪሾም ድረስ፣ በኢሰመኮ መቋቋሚያ ዐዋጅ መሠረት ምክትላቸው ወይዘሮ ራኬብ መሰለ ኃላፊነቱን እንደሚረከቡም ዶክተር ዳንኤል ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG