በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ተባብሶ የቀጠለው የስብአዊ መብት ጥሰት


በኢትዮጵያ ተባብሶ የቀጠለው የስብአዊ መብት ጥሰት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:34 0:00

የዩናዩትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሃገራትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በተመለከተ የሚያወጣውን ዓመታዊ ሪፖርት ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ በተለይም በኢትዮጵያ ባለፈው የአውሮፓውያኑ 2023 ዓ/ም ተፈጽመዋል የተባሉትን የመብት ጥሰቶች በዝርዝር አቅርቧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ወይም የመንግሥት ወኪሎች፣ ከሕግ ውጪ የዘፈቀደ ግድያ መፈፀማቸውን፣ በርካታ የሃገር ውስጥና የውጪ ሃገራት የሰብአዊ መብት ቡድኖችን ሪፖርት ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።

ግድያዎቹ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች እንዲሁም ትግራይን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የተፈጸሙ እንደሆነ አስታውቋል።

የምርመራ ጋዜጠኞች፣ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ተሰውረዋል ብሏል። መንግሥት በጋዜጠኞች እና በአንቂዎች ላይ እስሩን ባጠናከረበትም ወቅት፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መንግሥት የተሰወሩትን ግለሰቦች በተመለከተ የት እንዳሉ እንዲያሳወቅና ለፍርድ መቅረብ ካለባቸውም አስተማማኝ ማስረጃውን እንዲያቀርብ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ መጠየቁን አስታውሷል።

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መ/ቤት በሪፖርቱ የጠቀሰው እና በመንግሥት የተቋቋመው ነገር ግን በገለልተኝነት እንደሚሠራ የሚገለጸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን የሚመሩት ዋና ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት የተሰኘው ተቋም ዲሬክተር አቶ መሱድ ገበየሁ፣ በአሜሪካው ሪፖርት ላይ ያላቸውን አስተያየት እንዲሁም የመብት ድርጅቶች በመሬት ላይ የሚያከናውኑትን ተግባራት በተመለከተ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርገዋል።

ጥሰቶችን በማስቆም ረገድ፣ ጥሰቶቹንም በመፈጸም የሚከሰሰው መንግስት መውሰድ ያለበትን የመፍትሄ እርምጃዎች በተመለከተ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾቹ የሚሉት አለ።

[ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ]

XS
SM
MD
LG