No media source currently available
ስድሳ ስድስት ሰዎች ይዞ ከፓሪስ ወደ ካይሮ በመብረር ላይ የነበረው የግብፅ አየር መንገድ አውሮፕላን የተከሰከሰው ኬቴክኒካዊ ብልሽት ይልቅ በሽብርተኝ ጥቃት ይመስላል ሲሉ የግብፅ የአቪየሺን ሚኒስትር ተናገሩ። አራት ሰዓት በሚወስደው በረራ ዛሬ ሓሙስ ግብፅ አየር ክልል እንደገባ ከበረራ መቆጣጠሪያ ራዳር የተሰወረውን አውሮፕላን ስብርባሪ ለማግኘት በሜዲቴራኒያን ባህር ፍለጋ ቀጥሏል።