ዋሽንግተን ዲሲ —
ዩክሬይን፣ የአየር ክልሏ ለሩስያ አሮፕላኖች የተከለከለ መሆኑንና፣ የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጪ አገር የሚልከው ጋዝፕሮም (Gazprom) ተብሎ የሚጠራው የነዳጅ ካምፓኒ፣ ከእንግዲህ መላኩን እንደሚያቋርጥ በመግለጹ ዩክሬይንም ግዥውን እንደምታቆም አስታወቀች።
አፍቃሬ ምዕራባውያን የሆኑት ጠቅላይ የዩክሬይን ሚኒስትር አርሰኒ ያትሰንዩክ (Arseniy Yatsenyuk) ናቸው ይህን ዛሬ ይፋ ያደረጉት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ረቡዕ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ሲናገሩ፣ እርምጃው የተወሰደው በብሔራዊ ደኅንነት ጉዳይ የተነሳ መሆኑንና ሩስያም ባላት የትንኮሳ ጠባይ ነው ብለዋል።
ባለፈው ወር ዩክሬይን፣ የሩስያ አውሮፕላኖች አገሯ ላይ እንዳያርፉ አግዳ የነበረ ሲሆን፣ ሩስያ ግን የዩክሬይን አሮፕላኖች በክልሏ እንዲበሩ መፍቀዷ አይዘነጋም።