በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ዩናይትድ ስቴትስ የሩስያን ወረራ አትደግፍም" ምክትል ፕሬዚደንት ጆ ባይደን


ሩስያ፣ ክሬሚያን ወደራሷ ለመቀላቀል የምታደርገውን ሙከራ ዩናይትድ ስቴትስ በምንም መንገድ የማትደግፍ መሆኗን፣ ምክትል ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ለዩክራይን ምክር ቤት አባላት አረጋገጡ፤ በዚህም የፓርልማውን አባሎች ከፍተኛ አድናቆት አገኙ።

"ሩስያ የዩክራይንን ልዓላዊ ግዛት ወራለች" ያሉት ባይደን፣ "ግልጽ መሆን እሻለሁ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሩስያን ወረራ አትደግፍም፣ ከዚህ ቀደምም አልደገፈችም ወደፊትም አትደግፍም" ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ምክትል ፕሬዚደንት ባይደን ይህን ያሉት፣ በዩክራያን ያደረጉትን የሁለት ቀናት ጉብኝት ከማጠናቀቃቸው ቀደም ብለው ነው።

XS
SM
MD
LG