ዋሽንግተን ዲሲ —
በቅርቡ አንጎላ ውስጥ ምንነቱ በውል ባልታወቀ በሽታ ከሞቱ ሰዎች መካከል ስምንቱ ኤርትራውያን መሆናቸው ተገለጠ።
ሰሎሞን ገብረ ሥላሴ የተባሉ በዋና ከተማዋ ሉዋንዳ የሚኖሩ ኤርትራዊ ነጋዴ ለቪኦኤ ሲናገሩ የሞቱት ሰዎች በሙሉ በወባ መሰል ሃይለኛ ትኩሳት ተጠቅተው ነበር።
የአካባቢውን ሃኪሞች ለማነጋገር ሌጊዜው ባይቻልም ታማሚዎቹ ዴንጊ ትኩሳት ወይም የቆላ ንዳድ በሽታ ነው ተብለው በሓኪሞቻቸው ተነግሩዋቸው እንደነበር ተገልጹዋል።
በስምንቱ ኤርትራውያን ህልፈት በዚያ ባለው የኤርትራውያን ማህበረሰብ ዘንድ ከባድ ሃዘን አስከትሏል።
ሆኖም ይህ የቆላ ንዳድ በሽታ እያጠቃ ያለው የተወሰነ ማህበረሰብ ነው ለማለት የሚያበቃ መረጃ አለመኖሩን ከትግርኛ ክፍል ባልደረባችን ተወልደ ወልደ ገብርኤል ያገኘነው አክሎ አስገንዝቡዋል። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።